በኢራን ላይ ሚሳኤል የተኮሰችው ኢራን የአየር ክልሏን በመዝጋት የእስራኤልን ቀጣይ እርምጃ እየተጠባበቀች መሆኗን አስታውቃለች
እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ከባድ ጥቃት እንደምትሰነዝር ገለጸች፡፡
አንድ ዓመት ሊሆነው አምስተ ቀናት ብቻ የቀሩት የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ኢራን እና እስራኤል ወደ መደበኛ ጦርነት እንዳይገቡ ተሰግቷል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሊባኖሱ ሂዝቦላህ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተችው እስራኤል በዛሬው ዕለት በኢራን ሚሳኤል ተመታለች፡፡
የኢራን ጥቃት በመላው እስራኤል ያሉ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ እርጓል የተባለ ሲሆን ቴህራን ከ250 በላይ ሚሳኤል መተኮሷን አስታውቃለች፡፡
የሚሳኤል ጥቃቶቹ ኢላማቸውን እንደጠበቁ የገለጸችው ኢራን እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች ከባድ ጥቃት እንደሚጠብቃት አስጠንቅቃለች፡፡
ኢራን ወደ እስራኤል የባላስቲክ ሚሳዔሎችን መተኮስ ጀመረች
እስራኤል በበኩሏ በኢራን ሚሳኤሎች ስለደረሰባት ጉዳት እስካሁን ያላሳወቀች ሲሆን ከዛሬ አዳር ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ከባድ ጥቃት እንደምትፈጽም ዝታለች፡፡
ይሁንና እስራኤል በየትኞቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ ጥቃት እንደምታደርስ ከመናገር ተቆጥባለች፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ኢራን እስራኤልን እንዳጠቃች ገልጻ አብዛኞቹ ሚሳኤሎች ኢላማቸውን ሳይጠብቁ እና የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መክሸፋቸውን አስታውቃለች፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን የደህንነት አማካሪ ዙልቪያን እንዳሉት በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የአሜሪካ ባህር ሀይል ከኢራን የተተኮሱ አብዛኞቹን ሚሳኤሎች ማክሸፉን ተናግረዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በእስራኤል መዲና ቴልአቪቭ ባቡር ጣቢያ ለይ ሁለት ዜጎች በከፈቱት ተኩስ በትንሹ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ስምንት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸቸውን የሀገሪቱ ብዙሃ መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡