ኢራን ወደ እስራኤል የባላስቲክ ሚሳዔሎችን መተኮስ ጀመረች
ኢራን እስራኤልን ለመበቀል ወደ ቴል አቪቭ በርካታ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እና ሮኬቶችን መተኮስ ጀምራለች
በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል
ኢራን እስራኤልን ለመበቀል ወደ ቴል አቪቭ በርካታ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እና ሮኬቶችን መተኮስ ጀምራለች።
እስራኤል ባሳለፍነው አርብ ሌሊት በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት የሊባኖሱ ሄዝቦላህ መሪ ሼክ ሀሰን ናስራላህን መግደሏ ይታወሳል።
የሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጦ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱም አይዘነጋም፡፡
ይህን ተከትሎም በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነገሰ ሲሆን እስራኤል እና ሂዝቦላህ ከአየር ላይ ጥቃቶች በተጨማሪም በእግረኛ ጦር የታገዘ ውጊያ ጀምረዋል፡፡
የእስራኤልን ጥቃት ስታወግዝ የቆየችው ኢራን ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ተኩሳለች።
በመላው እስራኤል የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሳይረኖች እየተሰሙ ሲሆን፤ የፍንዳታ ድምጾች እና በሰማይ ላይ እሳቶችም እየታዩ እየታዩ ነው።
ኢራን ለእስራኤል "የወንጀል ተግባር" ምላሽ ትሰጣለች- የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢራን ጥቃት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ ካደረሰችው የባሰ ሊሆን ይችላልም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ጦር በእስራኤል ላይ ሊደርስ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን የገለጸ ሲሆን "ኢራን በቀጥታ ለምታደርሰው ጥቃት እና ሊወሰድባት ለሚችለው የአጸፋ እርምጃ የከፋ ሊሆን ይችላል" ሲል ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ለይ ባደረሰው ጥቃት ኢራን የቀጥታ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሐማሱ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሀኒየህ በቴህራን እያለ በኢራን መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሁለት ሳምንታት ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት የሂዝቦላህ ዋና ዋና መሪዎች ተገድለዋል፡፡
የሂዝቦላህ እና ሐማስ ዋነኛ አጋር እንደሆነች የሚገለጸው ኢራን እስራኤልን እንደምትበቀል በተደጋጋሚ ዝታለች፡፡