የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ118 እስከ 121 ብር መግዣ፤ ከ119 እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 20 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ጸደይ ባንክ ደግሞ አንድ ዶላርን በ120.9013 ብር ገዝቶ በ123.3193 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ነው ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን የጠቆመው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከትናንቱ የምንዛሬ ዋጋው በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ የዶላር መግዣ ዋጋን 120.0095 ብር አድርሷል። 122.4097 ብር የባንኩ የዶላር መሸጫ ዋጋ ነው።
ዳሽን ባንክ የጥቅምት 20 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከትናንቱ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጓል።
በዚህም አንድ ዶላርን በ120.0064 ብር እየገዛ በ122.4065 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።