ሄዝቦላ ናኢም ቃሲምን በሟቹ መሪ ነስረላህ ምትክ መሪ አድርጎ መምረጡን አስታወቀ
ቡድኑ ባወጣው መግለጫ ቡድኑ ዋና ጸኃፊ በሚመርጥበት አሰራር መሰረት የሹራ ምክርቤቱ የ71 አመቱን ቃሲምን መምረጡን ገልጿል
ቃሲም የሄዝቦላ ምክትል መሪ ሆኖ በ1991 የተመረጠው፣ በእስራኤል ሄሊኮፕተር ጥቃት በተገደለው በያኔው የሄዝቦላ መሪ አባስ አል ሙሳዊ ነበር
ሄዝቦላ ናኢም ቃሲምን በሟቹ መሪ ነስረላህ ምትክ መሪ አድርጎ መምረጡን አስታወቀ።
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ምክትል መሪ የነበረውን ናኢም ቃሲምን በእስራኤል የአየር ጥቃት በቤይሩት የተገደለውን የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ ነስረላህ ምትክ መምረጡን በዛሬው እለት አስታውቀዋል።
ቡድኑ ባወጣው የጽሁፍ መግለጫ ቡድኑ ዋና ጸኃፊ በሚመርጥበት አሰራር መሰረት የሹራ ምክርቤቱ የ71 አመቱን ቃሲምን መምረጡን ገልጿል።
ቃሲም የሄዝቦላ ምክትል መሪ ሆኖ በ1991 የተመረጠው፣ በእስራኤል ሄሊኮፕተር ጥቃት በተገደለው በያኔው የሄዝቦላ መሪ አባስ አል ሙሳዊ ነበር። ቃሲም ከእዚን ጊዜ ጀምሮ በምክትልነት ሲያገለግል ቆይቷል።
ነስረላህ መሪ ከሆነ በኋላ ከእስራኤል ጋር ያለው የድንበር ግጭት በተጋጋለበት በባለፈው አመት ጨምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ የቡድኑ ዋና ቃል አቀባይ ሆኖ ነበር።
ነስረላህ መስከረም 27 በቤይሩት ከተማ ዳርቻ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የተገደለ ሲሆን እሱን ይተካዋል ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ሀሽም ሰይፈዲንም ከሳምንት በኋላ ተገድሏል።
ነሰረላህ ከተገደለ ወዲህ ቃሲም ቡድኑ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚደረገውን ጥረት የደገፈበትን የመስከረም 8ቱን ጨምሮ ሶሰት በቴሌቪዥን የተላለፉ መግለጫዎችን ሰጥቷል።