የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ትኩረቱን በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ማስቆም እንጂ በሀይል የተያዙ ቦታዎች ላይ አያደርግም ተባለ
ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን በአንድ ቀን አስቆመዋለሁ ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል
የአሜሪካ እና ሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚስጥር እየተገናኙ መሆኑን ሞስኮ ገልጻለች
የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ትኩረቱን በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ማስቆም እንጂ በሀይል የተያዙ ቦታዎች ላይ አያደርግም ተባለ፡፡
ለአንድ ሳምንት ተብሎ የተጀመረው የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሜሪካ ለዩክሬን ከፍተኛ የገንዘብ እና ጦር መሳሪያ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ናት፡፡
አሜሪካ እስካሁን 64 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ድጋፍ ደረገች ሲሆን ይህ ገንዘብ በአሜሪካዊያን ህይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማድረሱን ተከትሎ የምርጫ መከራከሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡
ይህን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት የምርጫ ቅስቀሳ አጀንዳ ያደረጉት ሲሆን ጦርነቱን አንድ ቀን አስቆመዋለሁ ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ቅስቀሳቸው ለውጥ አምጥቶም ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ማሸነፋቸው ይፋ የሆነ ሲሆን የፊታችን ጥር ወር ለይ ስልጣን ይረከባሉ፡፡
ይሁንና ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከመረከባቸው በፊት ስለ ዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት መቆም ጉዳይ እየሰሩበት እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የሪፐብሊካን ፓርቲ ዋና ስልት ነዳፊ እና የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባል የነበሩት ብሪያን ላንዛ እንዳሉት አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር በሀይል ስለተወሰዱ የዩክሬን ግዛቶች አያተኩርም ብለዋል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር የሚያተኩረው ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነቱን እንዲያቆሙ ማድረግ ነው ያሉት ብሪያን እንደ ክሪሚያ ያሉ ቦታዎች ወደ ሩሲያ ተካለዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያም ሆነ የዩክሬን ጦር አሁን ባሉበት ሆነው ከ1 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር ርቀት ከሁለቱም ተፋላሚዎች ነጻ ሀኖ እንዲቆይ የሚል እቅድም ቀርቧል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ሩሲያ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኗን የሀገሪቱ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ሪያብኮቭ ተናግረዋል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ሩሲያ በሀይል ከያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች ጦሯን ካላስወጣች ሰላም እንደማይሰፍን በተደጋጋሚ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡