ቬክ መሀመድ ቢን ዛይድ እና የኩዌት አሚር በሁለትዮሽና የባህረ ሰላጤው ሀገራት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ቬክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኩዌት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
ፕሬዝዳንት ቬክ መሃመድ ቢን ዛይድ እናልኡካቸው ኩዌት ሲደርሱ በሀገሪቱ ኤሚር ሼከወ መሻል አል አህመድ አል ጃብር አላ ሳባህ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ቬክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና ከኩዌት ኤሚር ሼክ ኤሚር መሻል አል አህመድ በሁለትዮሽ እና በቀጠናዊ ጉዳዮ ለይም መክረዋል።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች ዘርፎች ያሉ ትብብሮች ያለበትን ደረጃ የገመገሙ ሲሆን፤ ይህም የሁለቱን ሀገራት ጥቅም እና ብልጽግና ባስጠበቀ መንገድ እያደገ መሆኑን አመላክዋል።
ቬክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና ሼክ መሻል አል አህመድ ሁለቱን ሀገራትና ወንድማማች ህዝቦችን የሚያስተሳስርና በፅኑ ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
በመከባበር፣ በመረዳዳት እና የጋራ ጥቅምን ባስከበረ መንገድ በቀጣናው ላይ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶችን አንድነት እና በትብብር መንፈስ ለመፍታት በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል።
በተጨማሪም ስለ ባህረ ሰላጤው ሀገራት፣ መካከለኛው ምስራቅ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም መምከራቸው ነው የተገለጸው።
በዚህም በጋዛ እና በሊባኖስ ያሉ ጦርነቶችን አንስተው የተወያዩ ሲሆን፤ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ማጠናከር እንዲሁም በአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ደንቦች መሰረት ለሲቪል ዜጎች ሙሉ ጥበቃ እንዲደረግ እንዲሁም ሰብአዊ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት የጋራ ጥረቶችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
የሊባኖስ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ እንዲጠበቅ ጠንካራ አቋም ያንጸባረቁ ሲሆን፤ ለሊባኖስ ህዝቦች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ያላቸውን ድጋፍ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሊባኖስ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በጋራ በመሆን ዓለም አቀፋዊ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለሲቪል ሰዎች ደህነንት የጋራ ጥበቃ እንዲደረግም ጥሪ አስተላልፈዋል።