በአለም ዙሪያ የሰሜን ኮሪያ ጦር አጋሮች እነማን ናቸው?
ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ልካልቸ የሚል ክስ ቀርቦባታል
የተመድ ማዕቀብ ሰለባ የሆኑት ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን በኑክሌር እና ባለስቲክ ሚሳይል ላይ ትብብር በማድረግ ይጠረጠራሉ
በአለም ዙሪያ የሰሜን ኮሪያ ጦር አጋሮች እነማን ናቸው?
ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ልካልቸ የሚል ክስ ቀርቦባታል።
ይህ ከተረጋገጠ ሀገሪቱ ከቬትናም ጦርነት ወዲህ ወታደሮች ወደ ውጭ ስትልክ የመጀመሪያ ይሆናል።
የሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ ወታደራዊ ትብብር ምን እንደሚመለሰል እንደሚከተለው ተዘርዝሯል።
ቬትናም
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ ታሪክ ኢንስቲትዩት ባሳተመው መጽሀፍ መሰረት ሰሜን ኮሪያ ከ1966-72 ድረስ ሚግ-17 የሚያበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብራሪዎችን ጨምሮ 1ሺ ወታደሮችን ወደ ሰሜን ቬትናም ልካለች።
ጡረታ የወጡ የቬትናም የአየር ኃይል ባለስልጣን እንደተናገሩት ከ1967-69 የሰሜን ኮሪያ አየር ኃይል 26 የአሜሪካ አውሮፕላኖችን መትቶ የጣለ ሲሆን 14 ወታደሮቹን ደግሞ አጥቷል።
ሰሜን ኮሪያ የፕሮፖጋንዳ ባለሙያዎቿን በመላክ እና በደቡብ ቬትናም በደቡብ ኮሪያ ወታደሮች ላይ ጥቃት በመክፈት ለቬትናም እገዛ አድርጋለች። ነገርግን ቬትናም ከምዕራባውያን ጋር ግንኙነቷን በማደሷ እና በ1992 ከደቡብ ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመጀመሯ ምክንያት በሰሜን ኮሪያ እና ቬትናም መካከል ያለው ግንኙነት ሊቀዛቀዝ ችሏል።
ግብጽ
በ1973 በተካሄደው የዮም ኪፑር ጦርነት ወቅት ሰሜን ኮሪያ፣ ሟቹ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ኢል ሰንግ እና ሁስኒ ሙባረክ በደረሱት ስምምነት መሰረት 1500 ወታደራዊ አማካሪዎችን እና 40 የአየር ኃይል አብራሪዎችን ልካልች።
ሊቢያ
ሁለቱ ሀገራት፣ ሊቢያ በሙአሙር ጋዳፊ በምትመራበት ወቅት ከሁለቱ በአንዳቸው ላይ ጥቃት በሚደርስባቸው ወቅት አንዳቸው ለሌላኛቸው ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የ10 አመት የጥምረት ስምምነት በ1982 ተፈራርመው ነበር።
ሶሪያ
ሶሪያ የረጅም ጊዜ የሰሜን ኮሪያ አጋር ስትሆን በሚሳይል እና በኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ላይም በጋራ ሰርተዋል። ሰሜን ኮሪያ ሶሪያ ውስጥ የሰራችው የፕሉቶኒየም ማብላያ እስራኤል በ2007 በፈጸመችው ጥቃት ወድሟል።
በ2013 የእስራኤል ሚዲያዎች በርካታ የሰሜን ኮሪያ ሄሊኮፕተር አብራሪዎች እና የከባድ መሳሪያ ተኳሾች ሶሪያ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ሲሉ ዘግበው ነበር። ፒዮንግያንግ ግን ይህን አስተባብለች።
በ2016 የሩሲያው ታስ ዜና አገልግሎት ሁለት የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ዩኒቶች በሽርን እግዘው እየተዋጉ መሆናቸውን ዘግበዋል።
ኢራን
የተመድ ማዕቀብ ሰለባ የሆኑት ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን በኑክሌር እና ባለስቲክ ሚሳይል ላይ ትብብር በማድረግ፣ ባለሙያዎችን እና ቁሳቁሶችን በመለዋወጥ ይጠረጠራሉ።
በ2ዐ15 የኢራን ተቃዋሚ የሆነ ቡድን ሰባት የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ባለሙያዎች ናታንዝ ኑክሌር ጣቢያን በ2002 መጎብኘታቸውን አጋልጧል።
ተመድ በ2021 ባወጣው መረጃም ሁለቱ ሀገራት የረጅም ርቀት ሚሳይል ለማምረት እና ወሳኝ እቃዎችን ለመለዋወጥ ትብብራቸውን ጀምረዋል።
አፍሪካ
ሰሜን ኮሪያ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ከዚምባቡዌ፣ ኡጋንዳ እና ከመሳሰሉት አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች የቆየ ወዳጅነት ነበራት። በ2011 የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጭ እንደገለጹት ሰሜን ኮሪያ ከ1999-2008 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደ ኮንጎ፣ አንጎላ፣ ሊቢያ እና ታንዛንያ ካሉ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ከ100 በላይ የመሳሪያ ሽያጭ ንግግሮችን አድርጋለች።
ነገርግን ሰሜን ኮሪያ በተጣለበት ጠንካራ የተመድ ማዕቀብ ምክንያት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት እየቀነሰ ሄዷል።