የሴራ ፖለቲካ ተንታኟ ላውራ ሉመር ከዶናልድ ትራምፕ ጋር መታየቷ ዲሞክራቶችን ለምን አሳሰበ?
ስደተኞችን ይጠላሉ የሚባሉት ሉመር የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ናቸው
ሉመር የመስከረም 1 የሽብር ጥቃት አሜሪካ ራሷ የፈጸመችው ነው በሚል ትንተናቸው ይታወቃሉ
የሴራ ፖለቲካ ተንታኟ ላውራ ሉመር ከዶናልድ ትራምፕ ጋር መታየቷ ዲሞክራቶችን ለምን አሳሰበ?
ከሁለት ወር በኋላ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳው የቀጠለ ሲሆን ከሰሞኑ ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሐሪስ መካከል በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ክርክር ላይ ከተገኙት መካከል ላውራ ሉመር አንዷ ነበረች፡፡
ይህች የ31 ዓመት ሴት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በምትሰጣቸው ትንታኔዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች አሏት፡፡
ይህች የሴራ ፖለቲካ ተንታኝ ዶናልድ ትራምፕ በሚያደርጓቸው የተለያዩ ሁነቶች ላይ በተደጋጋሚ መታየቷ አልፎ አልፎም በዶናልድ ትራምፕ የግል አውሮፕላን ሳይቀር ተሳፍራ ስትጓዝም ታይታለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተቀናቃኛቸውን ዶናልድ ትራምፕ ኮፍያ ለበሱ
ይህን ተከትሎ ላውራ ሉማር የሚዲያዎችን ትኩረት የሳበች ሲሆን የፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን አስተዳድር አሳስቧል፡፡
ሙራ ከ13 ዓመት በፊት በፈረንጆቹ መስከረም 9 ቀን 2011 ላይ በፔንታጎን መንትዮች ህጻ ላይ የደረሰው የሽብር ጥቃት በራሷ አሜሪካ የተቀነባበረ ነው ብላለች፡፡
የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ይህ የሴራ ፖለቲካ ትንታኔ ጥቃቱ በኦሳማ ቢንላደን በሚመራው አልቃይዳ የሽብር ቡድን መፈጸሙ በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል፡፡
ይህች ተንታኝ ከሰሞኑ ደግሞ በኦሂዮ የሚገኙ የሀይቲ ስደተኞች የቤት እንስሳትን እያረዱ እየበሉ ነው ማለቷን ተከትሎ ጉዳዩ ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡
በርካታ ሚዲያዎች በጉዳዩ ዙሪያ በሰሩት ማጣራት ድመት እና ውሻ እያረዱ ይበላሉ የተባሉት የሀይቲ ስደተኞች ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ የዘገቡ ቢሆንም የቴስላ እና ኤክስ ኩባንያ ባለቤቱ ኢለን መስክ ግን ጉዳዩ እውነት መሆኑን በተባለው ቦታ የምትኖር የአይን እማኝን ዋቢ በማድረግ ጽፈዋል፡፡
ኢለን መስክ በኤክስ (በቀድሞው ስሙ ትዊተር) ገጹ ላይ እንዳጋራው ከሆነ የሀይቲ ስደተኞች ድመት እና ውሾችን ከርሃብ እና አምልኮ ጋር በተያያዘ ያርዳሉ፡፡
የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ናት የምትባለው ላውራ ሉመር ዲሞክራቶች በስጋትነት የሚመለከቷት ሲሆን ዕጩ ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ ጥቁር አይደለችም፣ ምርጫውን አሸንፋ በነጩ ቤተ መንግስት ውስጥ ከገባች ግን አካባቢው በሕንዳዊን ምግቦች ሽታ ይታወዳል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በስደተኛ እና ሙስሊሞች ጠልነታቸው ይታወቃሉ የሚባሉት ላውራ ሉመር በምትሰነዝራቸው ወጣ ያሉ አስተያየቶች ምክንያት ፌስቡክን ጨምሮ ከተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ታግደዋል፡፡