ትራምፕ ከባይደን ይልቅ ካማላ ሀሪስ ለማሸነፍ ቀላል እንደሚሆኑላቸው ገለጹ
ከምርጫው መውጣታቸውን ያስታወቁት ባይደን፣ ካማላ ሀሪሰ የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ እንዲሆኑ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል
የባይደን መልሶ መመረጥ ጥያቄ ውስጥ የገባው ፕሬዝደንቱ ከትራምፕ ጋር ባለፈው ወር ባደረጉት ክርክር ደካሚ የሚባል አፈጻጸም ከሳዩ በኋላ ነው
የሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ከባይደን ይልቅ ካማላ ሀሪስ ለማሸነፍ ቀላል እንደሚሆኑላቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ ራሳቸውን ከመጭው ህዳር ምርጫ ካገለሉት ከዲሞክራቱ ፕሬዜደንት ጆ ባይደን ይልቅ ካማላ ሀሪስ ለማሸነፉ ቀላል ይሆናሉ ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።
በትናንትናው እለት ከምርጫው መውጣታቸውን ያስታወቁት ባይደን፣ ካማላ ሀሪሰ የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ እንዲሆኑ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
"ከጆ ባይደን ይልቅ ሀሪሰን ማሸነፍ ቀላል ነው" ሲሉ ትራምፕ ለሲኤንአን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ትራምፕ እና የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናቸው፣ ባይደን ፕሬዝደንት ሆነው መቀጠል አይችሉም የሚሉ ትችቾችን በማህበራዊ ሚዲያዎች አስተጋብዋል።
ባይደን የድጋሚ ምርጫ ቅስቀሳቸውን ለማቆም የተገደዱት ዲሞክራቶች በባይደን የአእምሮ ጤና እና ትራምፕ በማሸነፍ ችሎታቸው ላይ እምነት በማጣታቸው ነው። ባይደን ሀሪስ የፓርቲው እጩ እንዲሆኑ ድጋፋቸውን ችረዋል።
የባይደን መልሶ መመረጥ ጥያቄ ውስጥ የገባው፣ ፕሬዝደንቱ ከትራምፕ ጋር ባለፈው ወር ባደረጉት ክርክር ደካሚ የሚባል አፈጻጸም ከሳዩ በኋላ ነው።
ትራምፕ፣ ባይደን እንደማይወዳደደሩ ካሳወቁ በኋላ "ትሩዝ" በተባለው የራሳቸው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባይደን "ለፕሬዝደንት ለመወዳደር ብቁ አይደሉም" ብለዋል።
የተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሪፐብሊካን ሹሞች ባይደን ለፕሬዝደንትነት ብቁ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ትራምፕ እና ባይደን ብዙ ተቀራራቢ የሆነ የህዝብ ድጋፍ የነበራቸው ቢሆንም፣ ከክርክሩ በኋላ ግን ትራምፕ በጠባብ ድምጽ እየመሩ ናቸው።
የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ አማካሪዎች እንደተናገሩት ለካማላ ሀሪስ አይጨነቁም፤ ምክንያቱም ከማላ ሀሪስን ባይደን በተለይም በስተደኞች ጉዳይ እና በኑሮ ውድነት ጉዳይ ካሳዩት አፈጻጸም ጋር ማያያዝ ስለሚችሉ ነው።
ትራምፕ በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት የተደገባቸው የግድያ ሙከራ የምርጫውን ሂደት የበለጠ አነጋጋሪ አድርጎት ነበር።