ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው አነጋጋሪ በሆነው ፎቶ ዙሪያ አመሰግናለሁ ጆ ብለዋል
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተቀናቃኛቸውን ዶናልድ ትራምፕ ኮፍያ ለበሱ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጆ ባይደን የተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ ስም የተጻፈበትን ኮፍያ ለብሰው ታይተዋል፡፡
ከ23 ዓመት በፊት በፈረንጆቹ መስከረም 11 የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ተጎጂዎችን ለማሰብ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ እጩ ፕሬዝዳናቶቹ ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሀሪስም ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዚህ ጊዜ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ስም የተጻፈበትን ኮፍያ ጭንቅላታቸው ላይ አድርገው ታይተዋል፡፡
ይህ የፕሬዝዳንቱ ፎቶ በአጭር ጊዜ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ድርጊቱን ሆን ብለው እና የአሜሪካንን አንድነት ለማሳየት ብለው እንዳደረጉት ተገልጿል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በኤክስ አካውንታቸው ላይ ፎቶውን በማያያዝ “አመሰግናለሁ ጆ” ሲሉ ጽፈዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበረከቱ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ዲሞክራሲ ግልጽ ጠላት ነው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ዶናልድ ትራምፕም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን በርካታ ያልተገቡ ቃላትን በመጠቀም ሲዘልፏቸው ቆይተዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ወር ብቻ የቀረው ሲሆን የምርጫው እጩ የሆኑት ካማላ ሀሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ የፊት ለፊት ክርክር በማድረግ ለይ ናቸው፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ በተካሄደው የሁለቱ እጩዎች ክርክር ላይ ካማላ ሀሪስ የተሻለ ክርክር አድርገዋልም ተብሏል፡፡