አሜሪካውያን በተቋማት ላይ ያላቸው አመኔታ ከ40 ዓመታት ወዲህ ዝቅ ብሏል
አሜሪካዊያን ቡዶናልድ ትራምፕ ጉዳይ ለሁለት ተከፍለዋል።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቀናት በፊት በወንጀል ተከሰው እጃቸውን ሲሰጡ ፍትህ በደጋፊዎቻቸው እና በተቃዋሚዎቻቸው መሀል ተከፍላለች።
ማክሰኞ ኒዮርክ ማንሀተን ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ግርግር የተፈጠረ ሲሆን፤ የተለመደ ስም ማጥፋት እና ውዝግብ ከራሳቸው ከትራምፕም ታይቷል።
ነገር ግን ይህንን ጉዳይ እና ሌሎችንም የትራምፕ ምርመራዎች እየተመለከትን ነው የሚሉ ብዙ አሜሪካውያን "የፖለቲካ ነጥብ" ለማግኘት አንፈልግም ብለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ይልቁንም ዲሞክራሲያችን ፍትህ ይሰጠናል ብለው ተስፋ አድርገዋል።
ከመኖሪያ ቤታቸው ለአንድ ሰዓት በመኪና ተጉዘው የትራምፕን የክስ ሂደት በአካል ለማየት ማንሃተን ፍርድ ቤት የተገኙት ካርላ ሳምቡላ "በተለይ ጥቁር ቀለም እንዳለው ሰው [የፍትህ] ስርዓቱ በትክክል ይሰራል ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው" ብለዋል።
አሜሪካውያን እንደ ኮንግረስ፣ የቴሌቭዥን ዜና ማሰራጫ እና የፕሬዝዳንትነት መስሪያ ቤት ባሉ ተቋማት ላይ ያላቸው እምነት ከ40 ዓመታት ወዲህ በአማካይ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ መድረሱን ጋሉፕ የተባለ የምርምር ተቋም ገልጿል።
14 በመቶዎቹ ብቻ በወንጀል ፍትህ ስርዓቱ ላይ ትልቅ እምነት እንዳላቸው ተነግሯል። ይህም ከአስር ዓመታት በፊት የነበረው ግማሽ ያህል ነው ተብሏል።
ሀገሪቱ ለ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትራምፕ ግንባር ቀደም የሪፐብሊካን እጩ በሆኑበት ወቅት ትራምፕን የሚመለከቱ መዝገቦች ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ክስ መሆኑ ተነግሯል።
ትራምፕ ማክሰኞ በቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል።
የቀድሞ የዋይት ሀውስ ጠበቃ እና በሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የህግ ፕሮፌሰር የሆኑት ሪቻርድ ፔንተር "ህግ ህግ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካና ስልጣንም ነው" በማለት በግራና በቀኝ ያሉ ወገኖች የትራምፕ ክስ ላይ ያላቸውን እይታ ተችተዋል።
በመጪዎቹ ወራት የአሜሪካ የፍትህ ስርዓት አይን ውስጥ ይገባል።
ዶናልድ ትራምፕ ለወሲብ ፊልም ተዋናይነት አፍ ማዘጊያ ገንዘብ ከፍለዋል በሚል ከ30 በላይ ክሶች ቀርበውባቸዋል።