ዶናልድ ትራምፕ ሲ.ኤን.ኤን ላደረሰባቸው የስም ማጥፋት 475 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍላቸው ጠየቁ
ትራምፕ ሲኤኤን በ2020 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንድሸነፍ አድርጓል ብለዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ሲ.ኤን.ኤን ስሜን አጥፍቷል” ሲሉ ክስ መስርተዋል
የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲኤኤን ላደረሰባቸው የስም ማጥፋት 475 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸው ተገለፀ።
ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካው ሲኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የስም ማጥፋት ክስ መመስረታቸውም ተነገሯል።
በአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት ዶናልድ ትራምፕ “ሲኤንኤን ላደረሰብኝ የስም ማጥፋት ወንጀል 475 ሚሊየን ዶላር ካሳ ይክፈልኝ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ሚዲያው በተለይም በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አሜሪካውያን እንዳያምኑኝ ልዩ ቅስቀሳ በማድረግ በ2020 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንድሸነፍ አድርጓል ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር የሚጋጩት የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያን በተደጋሚ ሲወቅሱት ይሰማሉ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ2016 እስከ 2020 ድረስ ለአራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።
እንደፈርነጆቹ በ2020 በአሜሪካ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ጆ-ባይደን ድል ቢቀዳጁም አወዛጋቢው ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለታቸው ደጋፊዎቻቸው በርካታ ድርጊቶች ሲፈጽሙ እንደነበር ይታወሳል።
ደጋፊዎቻቸው በተለይም በዋሽንግተን የሚገኘውን የካፒቶል ህንፃ የወረሩበት ክስተት፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዴሞክራሲ ረዥም ርቀት ተጉዛለች በምትባለው ሀገረ አሜሪካ ይሆናል ብሎ ያልጠበቀው ትልቅ ግርምት የፈጠረ አጋጠሚ ነበር።