ዶናናድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “የአሜሪካ ጠላት ነው” አሉ
ትራምፕ መኖሪያ ቤታቸው በኤፍ.ቢ.አይ ከተበረበረ ወዲህ የመጀመሪያ ንግግር አድርገዋል
ጆ ባይደን “ጽንፈኛ” ያሏቸውን ዶናልድ ትራምፕን እና ደጋፊዎቻቸውን ማስጠንቀቀቸው ይታወሳል
የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “የአሜሪካ ጠላት ናቸው” ማለታቸው ተደምጧል።
ዶናልድ ትራምፕ በፎሎሪዳ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በኤፍ.ቢ.አይ ከተበረበረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።
ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ በተሰበሰቡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር “የመኖሪያ ቤት ብርበራው በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ነው” ብለዋል።
የ76 ዓመቱ ዶናልድ ትራምፕ ሁለት ሰዓት በፈጀው ንግግራቸው በአብዛኛው በመኖሪያ ቤታቸው የተደረገውን ብርበራ በመተቸት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በኋላ ላይ የዴሞካራት ተቀናቃኛቸው የሆኑትን ጆ ባይደንን ወደ መተቸት ተመልሰዋል።
በንግግራቸውም በ2020 የተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጭበርበሩን እና አሸናፊነትን እንደነጠቁ መናገራቸውም ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “የአሜሪካ ጠላት ናቸው” ሲሉ የተደመጡት ዶናድ ትራምፕ አሜሪካን ለመታደግም ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ቃል ገብተዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባሳለፍነው ሳምንት በፊላዴልፊያ ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸውን በጽንፈኝት መወንጀላቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "ጽንፈኛ የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ ዴሞክራሲን አደጋ ላይ ጥለዋል" ያሉ ሲሆን፣ በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ያሉ "ጨለምተኛ" ሀይሎችን ለመከላከል ሁሉም አሜሪካውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ ፕሬዝዳንት ጂ ባይደንን በተደጋጋሚ ሲወርፉ ይሰማል።
ትራምፕ ከወር በፊት ባደረጉት ንግግርም “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” ብለው እንደነበረ ይታወሳል።