የምርጫውን አሸናፊ ለማወቅ ተጨማሪ ጊዜን የሚፈልግ ሲሆን ሁለቱም እጩዎች የማሸነፍ እድላቸው እንዳለ ነው
በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ በሰፊ ልዩነት ካማላ ሀሪስን እየመሩ ናቸው
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ገኛሉ፡፡
ትራምፕ እስካሁን በተረጋገጡ የወኪል መራጮች ምርጫ አማካኝነት 230 በ210 ድምጽ እየመሩ ይገኛሉ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በ23 ግዛቶች ድል ሲቀናቸው ካማላ ሀሪስ ደግሞ በ13 ግዛቶች ድል ቀንቷቸዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
አስቀድሞ 270 የወኪል መራጮችን ድምጽ ያገኘ እጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይይናል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በቴክሳስ፣ፍሎሪዳ፣ ካሮሊና፣ ኦሂዮ፣አላባማ እና ሌሎችም ግዛቶች ላይ ድል ሲቀናቸው ካማላ ሀሪስ ደግሞ በካሊፎርኒያ፣ ማሳቹሴትስ፣ዋሽንግተን፣ ኮሎራዶ፣ኒዮርክ እና ሌሎች ግዛቶች ላይ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በቀሪ ግዛቶች ድምጽ እየተሰጠ ሲሆን ቀጣዮቹ ሰዓታት የምርጫውን አሸናፊ የሚወስኑ አይጠበቃል፡፡
ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በተጨማሪም የሁለቱ ምክር ቤት አባላት ምርጫም ጎን ለጎን እየተካሄደ ሲሆን ሪፐብሊካኖች አሁንም እየመሩ ይገኛሉ፡፡
የሴኔት ምክር ቤት አባላት ምርጫን ሪፐብሊካኖች ዲሞክራቶችን 50 ለ40 ሲመሩ ኮንግረስን ደግሞ 185 ለ154 በመምራት ላይ ናቸው፡፡