ፖለቲካ
ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ በጥብቅ ለምትፈልገው ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት ሰጡ
ኢድዋርድ ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት ለማግኘት ያለመከተው በፈረንጆቹ ህዳር 2020 ነበር
የአሜሪካ የምትፈልገው የ39 አመቱ ስኖውደን ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ በሩሲያ ተጠልሎ ይገኛል
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ለቀድሞ የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ሰራተኛ እና መረጃ አሳልፎ ለሰጠው ኤድዋርድ ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት እንዲሰጠው በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡
ስኖውደን በፈንጆቹ 2013 የአሜረካ መንግስት የጀርመኗን መሪ ጨምሮ የ35 ሀገራት መሪዎችን ስልክ እና ኢሜል ላይ ስለላ ማድረጓን አጋልጦ ነበር፡፡
ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት ከተሰጣቸው 70 የውጭ ሀገራት ዜጎች መካከል አንዱ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ኢድዋርድ ስኖውደን የሩሲያ ዜግነት ለማግኘት ያለመከተው በፈረንጆቹ ህዳር 2020 ነበር፡፡
መረጃ አሳልፎ በመስጠትና እና የመንግስትን ንብረት በመስረቅ የአሜሪካ የምትፈልገው የ39 አመቱ ስኖውደን ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ በሩሲያ ተጠልሎ ይገኛል፡፡ ስኖውደን ከሁለት አመት በፊት በሩሲያ ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ አግኝቷል፡፡
ምንም እንኳን የስኖውደን ደጋፊዎች፣ ስኖውደን ለሰዎች የሚቆረቆረ ሰው ነው ቢሉም አሜሪካ ግን የአሜሪካ ባለሙያዎችን እና ብሄራዊ ደህንነት ላይ ጉዳት አስከትሏል የሚል ክስ አቅርባለች፡፡
በአሁኑ ወቅት ለበርካታ አስርት አመታት በእስር ሊያቆየው የሚችል ክስ በአሜሪካ ተመስርቶበታል፡፡