አዲሱ የትራምፕ ማህበራዊ ሚዲያ ገበያው በጣም ተፈላጊ እና ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል
የቀዶሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው የማሕበራዊ ሚዲያ አማካይነት ወደ ማሕበራዊ ሚድያ ሊመለሱ መሆኑን አማካሪያቸው ተናግረዋል።
አማካሪያቸው ጄሰን ሚለር ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ዶናልድ ትራምፕን በሁለት በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ማሕበራዊ ሚድያ ተመልሰው እንደምናያቸው አስባለሁ" ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የሚከፍቱት የማህበራዊ ሚዲያ ፕላፎርም በማህበራዊ ሚዲያው ገበያው በጣም ተፈላጊ እና ጨዋታ ቀያሪ እንደሚሆንም አማካሪው ተናግረዋል።
ትራምፕ ምን አይነት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ የተባሉት አማካሪው፤ ለጊዜው ግልጽ ኤደልም በሚል ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን፣ ትርምፕ የሚሰሩትን ስራ ሁሉም ሰው ተጠባብቆ ማየት አለበት ብለዋል።
በጉዳዩ ላይም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታላላቅ ስብስባዎችን እያደረጉ መሆኑን አና አዲሱ ፐላትፎርም እጅግ በጣም ትልቅ እንደሚሆን ይጠበቃልም ብለዋል።
የቀዶሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ጥር ወር ከዋሽንግተን ዲሲው የካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር በተያያዘ ከትዊተር እና ፌስቡክ ገጽ መታገዳቸው ይታወሳል።
ትዊተር ከ87 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያፈራውን የትራምፕ ገፅ "ሌሎች ጥቃቶች ሊያነሳሳ ስለሚችል እስከመጨረሻው መዝጋቱም አይዘነጋም።