የትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ኮንግረስ አዳራሽ ሰብረው መግባታቸውን ተከትሎ 4 ሰዎች ተገድለዋል
ፕሬዝዳን ትራምፕ ባቀረቡላቸው ጥሪ ነው ደጋፊዎቻቸው ለተቃውሞ ወደ ኮንግረሱ በማምራት ያመጹት፡፡ በአመጹ ስብሰባው ቢስተጓጎልም ኮንግረሱ የትራምፕ ቡድን በ 5 ግዛቶች ያቀረበውን ቅሬታ ውድቅ አድርጓል፡፡ ሴኔቱና ኮንግረሱ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ ቀድሞ ይፋ የሆነውን ድምጽ በማጽደቅ ጆ ባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በዋሺንግተን ከሚገኘው የአሜሪካ ካፒቶል ህንፃ ፊት ለፊት በሚሰበሰቡበት ወቅት በፖሊስ መሳሪያ የተፈጠረው ፍንዳታ
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በዋሽንግተን የአሜሪካን ካፒቶል ደህንነት ከጣሱ በኋላ አንድ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊ በአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ
የትራምፕ ደጋፊዎች ከአሜሪካ ካፒቶል ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ ፖሊስ አንድን ሰው በቁጥጥር ስር ሲያውል
ተቃዋሚዎች ወደ አሜሪካ ካፒቶል ህንፃ (የኮንግረስ፣ የሴኔት እና የጠቅላይ ፍ/ቤት መሰብሰቢያ) ሲገቡ
የዩኤስ ካፒቶል የፖሊስ መኮንኖች አመጸኞችን ለመከላከል በተሰበረ በር አቅጣጫ ጠመንጃቸውን ደቅነው
የተቃውሞ ሰልፈኞች ወደ ምክር ቤት ለመግባት ሲሞክሩ የኮንግረሱ አባላት ሽፋን ለማግኘት እየተሯሯጡ
የትራምፕ ደጋፊዎች በአሜሪካ ካፒቶል ውስጥ ዘልቀው ከገቡ በኋላ የኮንግረሱ ሰራተኞች እራሳቸውን እየተከላከሉ
የትራምፕ ደጋፊዎች በአሜሪካ ካፒቶል ውስጥ ዘልቀው ከገቡ በኋላ የኮንግረሱ ሰራተኞች እራሳቸውን እየተከላከሉ
የካፒቶል ፖሊስ ቡድን በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ሲፈትሹ የኮንግረሱ ሰራተኞች እጃቸውን አንስተው
የዩኤስ ካፒቶል ፖሊስ በኮንግረሱ የጋራ ስብሰባ ወቅት ምክር ቤት የገቡ ተቃዋሚዎችን ሲቆጣጠሩ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የካፒቶልን ህንፃ ከወረሩ በኋላ ዴስክ ላይ ተቀምጣ
በአሜሪካ ኮንግረስ የ 2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ለማረጋገጥ የተደረገውን ስብበባ ለመረበሽ የትራምፕ ደጋፊች ወደ ውስጥ ለመግባት ከ ‹ካፒቶል ፖሊስ› ጋር ሲጋጩ
የተቃውሞ ሰልፈኛ በሴኔሩ በር ላይ ተንጠልጥሎ
ካፒቶል ሂል የገቡ የትራምፕ ደጋፊዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ
አድማ በታኝ ፖሊሶች ሰልፈኞችን ከአሜሪካ ካፒቶል ለማስወጣት ሲዘጋጁ
የተቃውሞ ሰልፈኞች የዩኤስ ካፒቶልን የህንፃ ቅጥር ጥሰው ከገቡ በኋላ የቆሰለ ሰልፈኛ
የዩኤስ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶልን ከወረሩ በኋላ የ 2020 የምርጫ ኮሌጅ ውጤትን ለማረጋገጥ የኮንግሬስ የጋራ ስብሰባን ሲመሩ
በስተመጨረሻም ውጤቱ ተረጋግጦ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ጸድቋል፡፡
ምንጭ ዘ ናሺናል