ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሰሯቸው ሁለት ስህተቶች ምን ምን ናቸው?
ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የተመለሱት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ አንድ ሳምንት ሆኗቸዋል
ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ስደተኞችን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ እውን ኖችን አሳልፈዋል
ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሰሯቸው ሁለት ስህተቶች ምን ምን ናቸው?
ከሁለት ወር በፊት በተካሄደው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ ከስድስት ቀናት በፊት በይፋ ስልጣን ተረክበዋል።
ከስምንት ዓመት በፊት 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ተሸንፈው ስልጣናቸውን ለጆ ባይደን አስረክበው ነበር።
ከአራት ዓመት ዕረፍት በኋላ ዳግም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ከገቡ በኋላ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ አዳዲስ ውሳኔዎችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።
ካሳለፏቸው ውሳኔዎች መካከልም በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የእስር ትዕዛዝ የተላለፈባቸው እስረኞችን መፍታታቸው አንዱ ነው።
የዶናልድ ትራምፕ ጓደኛንእና የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሊንደሲ ግራሀም ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ዶናልድ ትራምፕ ሁለት መሰረታዊ ስህተቶችን ወስነዋል ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ የተሳሳተ ውሳኔ አሳልፈዋል ከተባሉት ውሳኔዎች ውስጥ ግልጽ ወንጀል ፈጽመው በፍርድ ቤት ትፋተኛ የተባሉትን በይቅርታ መፍታት ወንጀለኞችን ያበረታታል ተብሏል።
ሌላኛው ዶናልድ ትራምፕ ስህተት ሰርተዋል የተባሉበት ጉዳይ የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ መንግሥት ያደርገው የነበረውን የደህንነት ጥበቃ ያስቀሩበት ነው።
የመንግስት ጥበቃ ከተነሳባቸው ባለስልጣናት መካከልም የቀድሞው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ እና የደህንነት አማካሪው ኮን ቦልተን ዋነኞቹ ናቸው።
ሁለቱ ባለስልጣናት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ወቅት ከኢራን የግድያ ሙከራ ሊፈጸም ይችላል በሚል ልዩ የደህንነት ጥበቃ ሲደረግላቸው ነበር።