የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከደህንነት መረጃ ታገዱ
አሜሪካ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ መሪዎች የሀገሪቱ ደህንነት መረጃዎች እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ህግ አላት
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/08/258-132514-whatsapp-image-2025-02-08-at-12.09.00-pm_700x400.jpeg)
ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ሲመጡ ዶናልድ ትራምፕ የሚታመን ሰው አይደለም በሚል መረጃው እንዳይደርሳቸው አግደዋቸው የነበረ ቢሆንም አሁን በተራቸው ታግደዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከደህንነት መረጃ ታገዱ
አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ መሪዎች በየዕለቱ ያሉ የአሜሪካ ደህንነት መረጃዎች እንዲያውቁት የሚፈቅድ ህግ አላት፡፡
ከአራት ዓመት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ተሸንፈው ስልጣን ለጆ ባይደን ካስረከቡ በኋላ ይህ አሰራር ከዶናልድ ትራምፕ ላይ ተሸሮ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በወቅቱ ዶናልድ ትራምፕ የሚታመኑ ሰዉ ባለመሆናቸው የአሜሪካ ዕለታዊ ደህንነት መረጃ ሊደርሳቸው አይገባም ሲሉ አግደዋቸው ነበር፡፡
በዳግም ምርጫ ድል ወደ ነጩ ቤተ መንግስት የተመለሱት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተራቸው ጆ ባይደን የአሜሪካ ዕለታዊ የደህንነት መረጃ ሊደርሰው አይገባም ሲሉ አግደዋቸዋል፡፡
ትራምፕና እስራኤል የጋዛ ነዋሪዎችን ለማስፈር ያቀዱት በየትኞቹ ሀገራት ነው?
“ጆ ተባረሃል፣ አንተ የአሜሪካ ሚስጢራዊ መረጃ ሊደርስህ የሚገባ ሰው አይደለህም” ሲሉ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ ባይደን በተጨማሪም የቀድሞ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ፣ የደህንነት አማካሪ ጆ ቦልተን እና ሌሎች ባለስልጣትንም አግደዋል፡፡