የዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ከነገ ጀምሮ ለተጠቃሚዎች እንደሚለቀቅ ተገለፀ
ግዙፎች የማህባራዊ ትስስር ድረ ገጾች የሆኑት ፌስቡክ፣ ትዊተርና ዩትዩብ ዶናልድ ትራምፕን ማገዳቸው ይታወቃል
'ትሩዝ ሶሻል' የማኅበራዊ ትስስር መተግበሪያ ከነገ ጀምሮ በአፕል ስቶር ላይ ማግኘት ይቻላል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ለተጠቃሚዎች ሊለቀቅ መሆኑ ታውቀዋል።
ሮይተርስ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት 'ትሩዝ ሶሻል' የማኅበራዊ ትስስር መተግበሪያ ከነገ ሰኞ ጀምሮ በአፕል ስቶር ላይ እንደሚለቀቅ ተመላክቷል።
ትሩዝ ሶሺያል የማህበራወ ትስስር መለቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ ከግዙፎቹ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ታግደው የቆዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መድረኩ እንዲመለሱ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የቀዶሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2021 ጥር ወር ከዋሽንግተን ዲሲው የካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር በተያያዘ ከትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩትዩብ መታገዳቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም ዶናድ ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲ.ኤም.ቲ.ጂ) 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ወደ መስራት መግባቱ ታውቋል።
ቲኤምቲጂ በፍላጎት መሠረት የሚሠራው 'ትሩዝ ሶሻል' የቪዲዮ አገልግሎት የመዝናኛ ፕሮግራምን፣ ዜናዎችን፣ ፖድካስቶችን እና ሌሎችንም ያሳያል ተብሏል።
'ትሩዝ ሶሻል' እስካሁን ካሉት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ እና መተግበሪያዎች በተሸለ የሰዎችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት ይጠብቃል ተብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የሚከፍቱት የማህበራዊ ሚዲያ ፕላፎርም በማህበራዊ ሚዲያው ገበያው በጣም ተፈላጊ እና ጨዋታ ቀያሪ እንደሚሆንም ይጠበቃል።