የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በዶናልድ ትራምፕ ላይ በእያንዳንዱ መዝገብ ላይ የአራት ዓመት እስር ውሳኔ ሊያስተላልፍ እንደሚችል ተገልጿል
የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በአሜሪካ ነውጥ እንዲጀመር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው ተባለ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2016 ምርጭ ከተመረጡ እና በስልጣን ላይ እያሉ የህግ ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ከተመሰረተባቸው ክሶች መካከልም ግብር መሰወር፣ አስገድዶ መድፈር፣ የግለሰቦችን ነጻነት መጋፋት፣ ሁከት ማነሳሳት እና ሌሎችም ዋነኞቹ ናቸው።
በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ሁሉ ጥፋተኛ የተባሉት ዶናልድ ትራምፕ የችሎት ውሎው ፖለቲካዊ ተጽዕኖ እንዳለበት ተችተዋል።
ይህን ተከትሎም በመላው አሜሪካ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በሀገሪቱ ሁከት እና አብዮት ለማስነሳት፣ በዳኞች እና ጠበቆች ላይ የግድያ ዛቻዎችን በተለያዩ መንገዶች እያካሄዱ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሳለፉ ዳኞችን መግደልን ጨምሮ የሀገሪቱ ፍትህ ስርዓት እንደማያዋጣ ጉልበት ብቸኛው አማራጭ እንደሆነ የሚገልጹ ይዘቶች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
ችሎቱ ጥፋተኛ በተባሉት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ሀምሌ 11 ቀን 2024 ላይ ቀጥሯል።
ዶናልድ ትራምፕ በእያንዳንዱ ክስ ከጊዜ ገደብ ቅጣት ጀምሮ እስከ 4 ዓመት እስር ይተላለፍባቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ይጠበቅባቸዋል።
የዲሞክራቶች እና ፕሬዝዳንት ባይደን ተጽዕኖ እየተደረገባቸው እንደሆነ የሚናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ፍትህ ስርዓት አደጋ ውስጥ እንዳለ የጠሱት ህግም እንደሌለ በመናገር ላይ ናቸው።
አሜሪካ የፊታችን ህዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የምታደርግ ሲሆን በተሰሩ የቅድመ ምርጭ ጥናቶች ዶናልድ ትራምፕ ከጆ ባይደን የተሻለ ተቀባይነት አላቸው።