ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ ያለው የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢዝነስ እንዲዘጋ አዘዙ
አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘው የንግድ ተቋም በሩሲያ ያለው ንግድ እንዲዘጋ ተወስኗል
የአውሮፓ ህብረት 223 ቢሊዮን ዶላር የሩሲያን ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ማገዱ ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ ያለው የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢዝነስ እንዲዘጋ አዘዙ፡፡
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ በአውሮፓ እየተካሄደ ያለው ያለው ጦርነት ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡
ይህ ጦርነት በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች እንዲጣሉባት ከማድረጉ ባለፈ ለዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ መናርም ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡
አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት ከማዕቀቡ ባለፈ የሩሲያ መንግስት እና ባለሀብቶች ንብረት የሖኑ ሁሉንም ሀብቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያገዱ ሲሆን ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሩሲያዊያንን ገንዘብ ማዋል ጀምረዋል፡፡
በተለይም የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ የታገዱ የሩሲያዊያን መንግስት እና ዜጎች ሀብትን ለዩክሬን መልሶ ግንባታ እንዲውል በመወሰን ላይ ይገኛሉ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ባሳለፍነው ሳምንት እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የሩሲያ ገንዘብ ውስጥ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለዩክሬን እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ሩሲያ ለህብረቱ ውሳኔ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በወቅቱ ገልጻ የነበረ ቢሆንም በሀገሯ ያሉ የምዕራባዊያን ሀገራትን ሀብት ማገድ ጀምራለች፡፡
የሩሲያ እና የኔቶ ወታደራዊ አቅም ሲነጻጸር ምን ይመስላል?
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ የሚንቀሳቀሰውን አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘው የንግድ ተቋም እንዲዘጋ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡
አሜሪካን ኤክስፕረስ የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሩሲያ ያለውን ንግድ ያቆመ ሲሆን ወደ ሩሲያ ቢዝነስ እንዲመዘገብ እንደተወሰነበት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ይሁንና አሜሪካን ቢዝነስ እንዴ እና እስከ መቼ ወደ ሩሲያ ሀብትነት እንደሚመዘገብ በዘገባው ላይ አልተገለጸም፡፡
በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በርካታ ምዕራባዊያን ሀገራት ኩባንያዎች ሞስኮን ለቀው ሲወጡ የተወሰኑት ደግሞ ንግዳቸውን ለማቆም ተገደዋል፡፡
ሩሲያ እነዚህ የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ስታደርግ የቆየች ሲሆን ስራ ያቆሙ ድርጅቶች በሩሲያዊያን ነጋዴዎች እንዲያዙ ግፊቶችን እና የተለያዩ ማበረታቻዎችን ስታካሂድ ቆይታለች፡፡