አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር የፔንታጎን አመራሮችን በገፍ ሊያባርር እንደሚችል ተገለጸ
የአሜሪካ ጦር ዋና አዘዦችን ጨምሮ በርካቶታ ጦር ጀነራሎች ከሃላፊነት ይነሳሉ ተብሏል
የቀድሞው የአሜሪካ ጦር አባል እና የፎክስ ኒውስ አዘጋጅ ፔቴ ሄግሴት አዲሱ የአሜሪካ ጦር አዛዥ እንደሚሆኑ ተገልጿል
አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር የፔንታጎን አመራሮችን በገፍ ሊያባርር እንደሚችል ተገለጸ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተደርገው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ መንግስታቸውን ለማቋቋም በሂደት ላይ ሲሆኑ የሚሾሟቸውን ሰዎች እያዘጋጁ ናቸው፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ጦር አባል የነበሩት እና በፎክስ ኒውስ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆኑት ፔቴ ሄግሴት አዲሱ የአሜሪካ ጦር ሃላፊ እንደሚሆኑ በዶናልድ ትራምፕ ታጭተዋል፡፡
ሄግሴት በዶናልድ ትራምፕ የቀረበላቸውን ሹመት እንደተቀበሉ የተገለጸ ሲሆን በአሜሪካ ጦር ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል ቃል ገብተዋል፡፡
ሄግሴት አክለውም በስልጣን ላይ ያሉት የሀገሪቱ ጦር አዛዦች አሜሪካ ደካማ እና እንዳትፈራ አድርገዋል ሲሉ ተችተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም የዶናልድ ትራምፕ ቡድን በፔንታጎን ያሉ የአሜሪካ ጦር አማራሮችን በገፍ ለማባረር እየተዘጋጁ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ትራምፕ ማርኮ ሩቢዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ
እንደ ዘገባው ከሆነ የፔንታጎን ዋና አዛዥ እና በስራቸው ያሉ የሾሟቸው ሌሎች ወታደራዊ አማራሮችን ዶናልድ ትራምፕ በማባረር አዲስ አዛዦችን የማምጣት ፍላጎት አላቸው፡፡
ይሁንና አሜሪካ በዩክሬን እና በመካከለኛው ምስራቅ እየተሳተፈችበት ያለው ጦርነት ባለበት በዚህ ወቅት ወታደራዊ አዛዦችን በገፍ ላታባርር ትችላለችም ተብሏል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ማርክ ሩቢዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ቶም ሀውክ የድንበር ጉዳዮች፣ ኤሊዝ ስቴፋኒክን ደግሞ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል፡፡