ትራምፕ በድንገት የሚከፈቱ ጅምላ ተኩሶች ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ጭምር የሚያያዙ ናቸው ብለዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸው መምህራንን እንድታስታጥቅ ጠየቁ፡፡
ትራምፕ በቴክሳስ የተፈጸመውን ሰሞነኛ ግድያ በተመለከተ ብሔራዊ የጦር መሳሪያዎች ማህበር (NRA) ባካሄደው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸው ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ችግሮች እና የአእምሮ ሕመምን ተደጋግመው በትምህርት ቤቶች ለተፈጸሙ ድንገተኛ ለግድያዎች ምክንያት አድርገው አስቀምጠዋል፡፡
በእርሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን እንዲህ ዐይነቱን ችግር ለመቅረፍ ብዙ መስራታቸውን በመጠቆምም የተካቸውን አዲሱን የባይደን አስተዳደር ወቅሰዋል፡፡
አስተዳደሩ እንዲህ ዐይነቶቹን መሰል ችግሮች ለማስቆም መምህራንን እንዲያስታጥቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” አሉ
"ለዩክሬን የምንሰጠው 40 ቢሊዮን ዶላር ካለን በቤታችን የራሳችንን ዜጎች ደህንነት ለመጠበቅ ከዚህም በላይ ማውጣት አለብን"ም ነው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያሉት፡፡
"የታጠቀን መጥፎ ሰው ማስቆም የሚችለው የታጠቀ ጥሩ ሰው ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል የ79 ዓመቱ አዛውንት፡፡
ትምህርት ቤቶች ዒላማ ውስጥ ሊገቡ በማይችሉበት ሁኔታ መገንባት እንዳለባቸውም በማሳሰብም ጦር መሳሪያዎች ከትምህርት ቤቶች እንዲርቁ ጠይቀዋል፡፡
ከሰሞኑ በቴክሳስ ኡቫልዴ ከተማ በሚገኝ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ሁለት መምህራንን ጨምሮ 20 ገደማ ህጻናት ተማሪዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡