ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ምርጫ ካሸነፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ ተገለጸ
አሜሪካ ከ11 ሚሊዮን በላይ ሰነድ አልባ ስደተኞችን አስጠልላለች
ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት በነበሩባቸው አራት ዓመታት ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ስደተኞችን ከአሜሪካ አባረዋል
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ምርጫ ካሸነፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ የፊታችን ህዳር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ እጩዎች በምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ናቸው፡፡
የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ሊያሸንፉ ግምት ከተሰጣቸው እጩዎች መካከል ዋነኛው ናቸው፡፡
የዶናልድ ትራምፕ አጣማሪ የሆኑት ጄዲ ቫንስ በምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ባደረጉት ንግግር በአሜሪካ የሚኖሩ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በአሜሪካ አሁን ላይ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ11 ሚሊዮን በላይ ሰነድ አልባ ስደተኞች ያሉ ሲሆን የዶናልድ ትራምፕ ቡድን ምርጫውን ካሸነፈ እነዚህን ስደተኞች በሀይል እንደሚያባርሩ ተገልጿል፡፡
ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2020 ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ ዶናልድ ትራምፕ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ስደተኞችን በሀይል ወደ ሀገራቸው አባረዋል፡፡
የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ኢራንን በመረጃ ምንተፋ ከሰሰ
በፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የአስተዳድር ዘመን ሶስት ሚሊዮን ስደተኞች በሀይል ከአሜሪካ የተባረሩ ሲሆን በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ስደተኞችን በሀይል አባረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ እና ቡድናቸው ሰነድ አልባ ስደተኞች የአሜሪካዊያንን የስራ እድል ከመቀማት ባለፈ ለወንጀሎች መበራከት ምክንያት ሆነዋል ብለው ምናሉ ተብሏል፡፡
አሜሪካ በግዛቷ ያሉ ስደተኞችን በሀይል ለማባረር ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚጠይቃት የተገለጸ ሲሆን ወጪው በመብዛቱ ምክንያት በሀይል የሚባረሩ ስደተኞች ቁጥር አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡