ለጋሾች 1.7 ቢሊዮን ዶላር ለሶስት ሀገራት ለገሱ
ቃል የተገባው ገንዘብ በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊና በኒጀር ለሚገኙ 10 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ የሚውል ነው
ከ20 በላይ ለጋሽ ሀገራት በሰብአዊ ቀውስ ለሚታመሱት ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ለዚህ አመት የሚውል 1ቢሊዮን ዶላር መድበዋል
ከ20 በላይ ለጋሽ ሀገራት በሰብአዊ ቀውስ ለሚታመሱት ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ለዚህ አመት የሚውል 1ቢሊዮን ዶላር መድበዋል
ከ20 በላይ ለጋሽ ሀገራት በሰብአዊ ቀውስ ለሚታመሱት ሶስት የአፍሪካ ሀገራት 1 ቢሊዮን ዶላር ለዚህ አመት የሚሆንና የ700 ሚሊዮን ዶላር ለፈረንጆቹ 2021ና ከዚያ ቀጥሎ ላለው ጊዜ የሚውል ለመስጠት ቃል መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ እንደገለጹት ቃል የተገባው ገንዘብ በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊና በኒጀር ለሚገኙ 10 ሚሊዮን ሰዎች የተያዘው የፈረንጆቹ አመት እስከሚያልቅና ለሚቀጥለው አመት ለምግብ፤ ለጤና፤ ለመጠለያና ለትምህርት እንዲሁም በጾታዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑት ድጋፍ ይውላል ተብሏል፡፡
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከለጋሾ ጋር በነበራቸው ቆይታ ማእከላዊ የሳህል ቀጣና በመሰባበር ላይ ነው፤ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎትም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡
ዋና ጸኃፊው እንዳሉት በቀጣናው ያለው የጸጥታ ሁኔታ በየቀኑ እየተባባሰ ነው ብለዋል፡፡ ጥቃት በተለይም የህጻናትና የሴቶች ጥቀት እየተጨመረ ይገኛል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ የሰዎች ኑሮ እያመሰቃቀለው ነው፤ የኮሮና ቫይረስም ማመሰቃቀሉን ገልጸዋል፡፡
አለም ቀፋዊ ችግሮች በሳህል ቀጣና ተሰባስበዋል፤ እነዚህን ችግሮች መፍታት ያስፍልጋል ብለዋል፡፡