አይኤም ኤፍ የአፍሪካ ሀገራት የ345 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍተት አለባቸው አለ
ሀገራቱ ከአጠቃላይ ገቢያቸው 2.5 በመቶ ህዝባቸውን ለመርዳት ሟዋል እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል
ኮሮና የአፍሪካ ሀገራት እስከ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ የ345 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍት እንዲያጋጥማቸው አድርጓል ተባለ
ኮሮና የአፍሪካ ሀገራት እስከ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ የ345 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍት እንዲያጋጥማቸው አድርጓል ተባለ
ሀገራትና ተቋማት የኮሮና ቫይረስ የኢኮኖሚ ጉዳት ያደረሰባቸውን ሀገራት መርዳት አለባቸው ያለው አይኤምኤፍ የአፍሪካ ሀገራት እስከ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ የ345 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍት ያጋጥማቸዋል ብሏል፡፡
የአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲና ጂዎርጂቫ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የአፍሪካ ሀገራት የሀገራቸውን አጠቃላይ ገቢ 2.5 በመቶ ህዝባቸውን ለመርዳ ሟዋል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሯ እንደገለጹት ከሆነ የግል ብድርም እየቀነሰ ነው ብለዋል፡፡
“ወረርሽኙ በቀላሉ የሚያልቅ አይደለም፤ ሁላችንም፣ ሀገራትና ተቋማት የወረርሽኙን ቀጣይ ችግር ለመቋቋም መስራት አለብን” ብለዋል፡፡
ክርስቲና ጂዎርጂቫ እንደገለጹት ምንምእንኳን ማሻሻያዎች ቢደረጉም የአፍሪካ ሀገራት እስክ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ 1.2 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፤ ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ብድር ያለባቸው ሀገራት ብድር በመክፈልና ተጨማሪ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎቶች ወጭ ምርጫ ውስጥ እንዲገቡ ተገደዋል ብለዋል፡፡
ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች የሚገኘው ብድር ከሚፈለገው ከሩብ በታች ነው፤ ከግል ተቋማት የሚገኘው ብድርም አነስተኛ በመሆኑ የፋይናንስ ክፍተቱ የኮሮና ወረርሽኝ፣ የሸቀጦች ዋጋ መውረድ እና የአምበጣ ወረርሽኝ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካውያንን ለረሃብ አደጋ ማጋለጡን የአለም ባንክ ግምት ያሳያል፡፡እንዲፈጠር አድርጎታል፡፡ ኤይኤም ኤፍ አባላቶቹ አዲስ የብድር ለመስጠት ቃል እንዲገቡ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡