በተከበበችው የሱዳኗ ከተማ መነሻው ሚስጥራዊ በሆነ ህመም በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ
ከተማዋ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የበቀል እርምጃ ከተወሰደባቸው በአል-ገዚራ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት አንዷ ነች ተብሏል
በሱዳን የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ በትብብር መፈንቅለ መንግስት በፈጸሙ ጀነራሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል
በተከከበችው የሱዳኗ ከተማ መነሻው ሚስጥራዊ በሆነ ህመም በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ።
በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በተከበበችው የሱዳኗ አል-ሂላሊያ ከተማ መነሻው ሚስጥራዊ በሆነ ህመም በሽታ 73 ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን የዶክሮች ህብረት ባለፈው ረቡዕ እለት አስታውቋል።
ከተማዋ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡ ወደ ሱዳን ጦር ከተቀላቀለ ወዲህ የበቀል እርምጃ ከተወሰደባቸው በአል-ገዚራ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት አንዷ ነች ተብሏል።
በሱዳን፣ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር እና በሱዳን ጦር መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአለም አስከፊ የሚባለውን የሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል። በጦርነቱ ከ11 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቤታቸው የፈናቀሉ ሲሆን ብዙዎች የረሀብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
በሌላው አል ገዚራ ክፍል በፈጥኖ ደራሽ በሚተኩሰው ከባድ መሳሪያ ብዙዎች እየተገደሉ ሲሆን በሂላሊያ በተቅማጥ በሽታ እየታመሙ በአካባቢው የሚገኘውን ሆስፒታል ማጥለቅለቃቸውን ሮይተርስ ሶሰት ሰዎችን እና ማህበሩን ጠቅሶ ዘግቧል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በቦታው ያለውን ኢንተርኔት በማጥፉቱ በሽታው በምን ምክንያት እንደተነሳ ለማወቅ አልተቻለም። አንድ ነዋሪ ሶስት ቤተሰቦቹ መሞታቸውን እና ይህንንም ያወቀው ሌሎች ኢንተርኔት ወደሚሰራበት ቦታ ማምለጥ ከቻሉ በኋላ መሆኑን ለሮይተርስ ተናግሯል።
ሰዎች ከዘህ ቦታ ኢንተርኔት ወዳለበት ቦታ ለማሄድ ኬላ በሚጠብቁ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወታደሮች ብዙ ገንዘብ ለመክፈል እንደሚገደዱም ዘገባው ጠቅሷል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር ባለፈው ጥቅምት 29 በከተማዋ አምስት ሰዎችን መግደሉን እና ከተማዋን መክበቡን ነዋሪዎች ተናግረዋል። 50ሺ ሰው ይኖርባት የነበረችው እና ወደ ሱዳን ጦር የተቀላቀለው የጦር አዛዥ አቧግላ ኬይካል የትውልድ ቦታ የሆነችው ከተማ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባት ከተማ ነበረች።
አሁን ላይ የከተማዋ ገበያዎች እና መጋዘኖች መዘረፋቸውን ሮይተርስ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከያሌ የሰብአዊ ላብ የተወሰዱ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር በግዛቷ የበቀል እርምጃ መውሰድ ከጀመረበት ከባለው ጥቅምት ጀምሮ በገዚራ ከተማ በርካታ ቦታዎች የቀብር ቦታዎች ጨምረዋል።
አዝራቅ በተባለ ቦታም የግብርና ምርቶች ተቃጥለዋል።
በሱዳን የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ በትብብር መፈንቅለ መንግስት በፈጸሙ ጀነራሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል።