ዩክሬን የሩሲያ ኃይሎች በዛፖሪዝሂያ ከተማ ላይ በፈጸሙት ጥቃት 17 ሰዎችን ገደሉ አለች
የዩክሬን ባለስልጣናት ይህን በሉ እንጅ ሩሲያ ጥቃቱን በተመለከተ እስካሁን ያለችው ነገር የለም
የዩክሬን ጦር ኃይሎች አዛዥ ፤የሩስያ ወታደሮች በዛፖሪዝሂያ ከተማ ላይ በሌሊት ጥቃት ማድሳቸው ገልጸዋል
ዩክሬን የሩሲያ ኃይሎች በዛፖሪዝሂያ ከተማ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደሉ ስትል ከሰሰች፡፡
የዩክሬን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የሩስያ ወታደሮች በደቡብ ምስራቋ ዛፖሪዝሂያ ከተማ በአንድ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት ማድሳቸው ገልጸዋል፡፡
የዩክሬን ጦር ማዕከላዊ እዝ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍም " የሩሲያ ወራሪዎች በሌሊት የመኖሪያ ህንጻዎችን እና የሲቪል መሰረተ ልማትን በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ፈጽመዋል” ብሏል፡፡
የከተማዋ የመንግስት ጸሃፊ አናቶሊ ኩርቴቭ በአንድ ሌሊት በደረሰ ጥቃትበደረዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።
አናቶሊ ኩርቴቭ በተሌግራም ባጋሩት መረጃ "በዛፖሪዝሂያ ላይ በአንድ ሌሊት በተፈጸመ የሚሳዔል ጥቃት ምክንያት በከተማው በሚገኙ የመኖሪያ አካባቢዎች የሚገኙ የአፓርትመንት ህንጻዎች እና መንገዶች ተጎድተዋል" ብለዋል፡፡
አስካሁን ባለው መረጃ 17 ሰዎች ሞተዋል ሲሉ መናገራቸውም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ባለስልጣናት ይህን በሉ እንጅ በሩሲያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
የዩክሬን ጦር ባለፈው ወር መጀመሪያ በካርኪቭ ክልል የጀመረውን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ በዩክሬን ጦር ሜዳ ላይ ሩሲያ ጫና እየበዛባት ነው።
በዚህም በቅረቡ አራት የዩክሬን ክልሎችን ለዘላለሙ ጠቅላያለሁ ስትል የነበረችው ሩሲያ መሬት ላይ ያለው ሁኔታ የጦር መሪዎቿን ኩፉኛ ማስተቸቱን ተከትሎ በዩክሬን የጀመረችውን ልዩ ዘመቻ የሚመራ ጄኔራል ሾማለች፡፡
አሁን በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዘመቻውን እንዲመሩ የተሸሙት ደግሞ የአየር ሃይል ጄኔራል የሆኑትን ሰርጌይ ሱሮቪኪ መሆናቸው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ማንም ቢሆን ሱሮቪኪን የሚተካው ማን እንደሆነ አልገለጸም፡፡
ሹመቱ በሞስኮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሶስተኛው ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ነው ተብሏል፡፡