ሩሲያ በዩክሬን ምድር ምዕራባውያን ጋር እየተዋጋች እንደሆነ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚንስትር ገለጹ
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 7 ወራትን አስቆጥሯል
የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት እና ከ200 በላይ የሲቪል ሳተላይቶች ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ ነው
ሩሲያ በዩክሬን ምድር ምዕራባውያን ጋር እየተዋጋች እንደሆነ የሩሲያ መከላከያ ሚንስትር ሰርጊ ሼጉ አስታውቀዋል።
ከሰባት ወር በፊት የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሀያላን ሀገራት ጎራ ለይተው ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።
በዚህ ጦርነት ሩሲያ እንድትሸነፍ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በማስታጠቅ ላይ ናቸው።
ዩክሬንም ከነዚህ ሀገራት የሚደረግላትን የጦር መሳሪያ በመጠቀም በሩሲያ ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን መልሳ በማስለቀቅ ላይ ስትሆን አሜሪካ የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰጧት ጠይቃለች።
ይህንን በተመለከት አስተያየት የሰጡት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሼጉ፤ ሀገራቸው በዩክሬን እያደረገች ባለው ጦርነት በተዘዋዋሪ ከምእራባውያን ጋር ውጊያ ላይ መሆኗ አሰታውቀዋል።
ሚንስትሩ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት በጦርነቱ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እያድረጉ እንሆነ አስታውቀዋል።
እንዲሁም ከ200 በላይ የሲቪል ሳተላይቶች ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ መናገራቸውን ሩሲያን ቱዴይ ዘግቧል።
ሚንስትሩ አክለውም እስካነ በተደረገው ጦከ150 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መግደላቸው እና 6 ሺህ ገደማ የሩሲያ ወታደሮች ደግሞ እንደተገደሉባቸውም ገልጸዋል።
ሩሲያ ከዚህ ቀደም ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የጦር መሳሪያ ማስታጠቅ ማለት ቀይ መስመርን ማለፍ ነው ስትል በተደጋጋሚ ማስጠንቀቋ ይታወሳል።