እስራኤል በሶሪያ በፈጸመችው ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን መገደላቸው ተገለጸ
የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ እስራኤል የፍልሰጤሙ ታጣቂ ቡድን መሾጎባቸዋል የምትላቸውን በሶሪያ ውስጥ ያሉ ቦታዎችን መደብደቧን ቀጥላበታለች
የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እስራኤል እና ታጣቂ ቡድኑ በፈጸሙት ጥቃት ንጹሃን እና ወታሮች መገደላቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
እስራኤል በሶሪያ በፈጸመችው ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
እስራኤል በሰሜን ሶሪያ በምትገኘው የአሌፖ ከተሜ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አምስት የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ 38 ሰዎችን መግደሏን ሮይተርስ ምንጮችን ዘግቧል።
የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እስራኤል እና ታጣቂ ቡድኑ በፈጸሙት ጥቃት ንጹሃን እና ወታሮች መገደላቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንደገለጸው እስራኤል በፈጸመችው የአየር ድብደባ አሌፖ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ቦታዎችን ኢላማ አድርጋለች።
የአየር ጥቃቱ የሽብር ድርጅቶች ከእድሊብ ከተኮሱት የድሮን ጥቃት ጋር በመገጣጠሙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ብሏል ሚኒስቴሩ።
ነገር ግን ሚኒስቴር የሟቾች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ እና ግድያ የተፈጸመው በእስራኤል የአየር ጥቃት ይሁን በታጣቂዎቹ ግልጽ አላደረገም።
"ጥቃቱ በንጹሃን እና በወታደሮች ላይ መስዋትነት አስከትሏል፤ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል" ብሏል ሚኒስቴሩ።
የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት ከተጀመረበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ እስራኤል የፍልሰጤሙ ታጣቂ ቡድን መሾጎባቸዋል የምትላቸውን በሶሪያ ውስጥ ያሉ ቦታዎችን መደብደቧን ቀጥላበታለች።
በሶሪያ የእርስበእርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ከ2011 ወዲህ የሶሪያው መሪ በሽር አላሳድን የምትደግፈው ኢራን ተጽዕኖዋ እያደገ መጥቷል።
ይህ እሰራኤል ሶሪያ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች ቦታ እንዲኖራቸው ያደርጋል በሚል ስጋት እንዲያድርባት አድርጓል።