ተጠባቂው የቦክስ ፍልሚያ በጃክ ፖል አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የቀድሞው የቦክስ ስፖርተኛ ማይክ ታይሰን እና ጃክ ፖል በአሜሪካ ቴክሳስ ዛሬ ሌሊት ተፋልመዋል
ብዙም አጓጊ ያልነበረውን ውድድር በሶስቱም ዙሮች ታይሰን ተሸንፏል
ተጠባቂው የቦክስ ፍልሚያ በጃክ ፖል አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
በቦክስ ስፖርት ዘርፍ ስኬታማ ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ማይክ ታይሰን ከወጣቱ ጃክ ፖል ጋር ዛሬ ሌሊት በቴክሳስ ተፋልመዋል፡፡
ከቦክስ ስፖርቱ ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነው ፖል በእድሜ አባቱ ከሆነው ዝነኛው ማይክ ታይሰን ጋር ተፋልሟል፡፡
የብዙዎችን ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ውድድር ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ማይክ ታይሰን በሆድ ህመም መጠቃቱን ተከትሎ ለዛሬ ተራዝሞ ነበር፡፡
ይህን ውድድር ጃክ ፖል ያሸነፈ ሲሆን በሶስቱም ዙሮች ማይክ ታይሰን ድል ሳይቀናው ቀርቷል፡፡
ጃክ ፖል ከውድድር መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው አስተያየት በዓለም ላይ ያለ የትኛውም ቦክሰኛን ለመግጠም ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡
የ58 ዓመቱ የቀድሞው የቦክስ ስፖርተኛ እና ማይክ ታይሰን ካደረጋቸው የቦክስ ውድድሮች ውስጥ 19 ፍልሚያዎችን ያለሽንፈት ያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 12ቱ የመጀመሪያው ዙር ላይ በዝረራ ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡
ማይክ ታይሰን ሳይታሰብ በ20 ዓመቱ ጃማይካዊ ትሬቨር ቤርቢክ መሸነፉ የዓለምን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡
ከ20 ዓመት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰው ማይክ ታይሰን ዳግም ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን ከእንግዲህ ወደ ውድድር ላይመለስ ይችላልም ተብሏል፡፡