ሩሲያ በዩክሬን የኃይል መሰረተልማት ላይ ከባድ የሚሳይል ጥቃት ፈጸመች
ሩሲያ ከነሐሴ ወዲህ በፈጸመችው መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት የዩክሬን የኃይል መሰረተልማቶችን ኢላማ ማድረጓን ባለስልጣናት ገልጸዋል
ሚኒስትሩ ጥቃቱን ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ንግግር ላደረጉት ኦላፍ ሾልዝ መልስ ነው ሲሉ ገልጸውታል
ሩሲያ በዩክሬን የኃይል መሰረተልማት ላይ ከባድ የሚሳይል ጥቃት ፈጸመች።
ሩሲያ ከነሐሴ ወዲህ በፈጸመችው መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት የዩክሬን የኃይል መሰረተልማቶችን ኢላማ ማድረጓን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ዩክሬን ችግር ውስጥ በገባው የኃይል መሰረተልማቷ ላይ የሚደርሰው ለሳምንታት የቆየው ጥቃት ለረጅም ጊዜ የኃይል መቋረጥ እና ወሳኝ በሆነ ሰአት የስነ ልብና ጫና ያስከትላል የሚል ስጋት አድሮባታል።
"ሌኛው በኃይል መሰረተልማት ላይ ያነጣጠረ ግዙፍ ጥቃት እየተካሄደ ነው። ጠላት በመላው ዩክሬን የኃይል ማመንጫዎችን እና የማስተላለፊያ መስመሮችን እያጠቃ ነው" ሲሉ የዩክሬን የኢነርጂ ሚኒስትር ጀርመን ጋሉሽቸንኮ ተናግረዋል።
ሌሊቱን የአየር ኃይሉ በኪቭ ከተማ ድሮኖችን ለማክሸፍ ሲተኩስ እና ከፍተኛ ፍንዳታ ሲሰማ ነበር ተብሏል።የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም።
ባለስልጣናት ጉዳት ለመቀነስ በሚል በኪቭ እና በዙሪያዋ ያሉ ግዛቶች ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ያሉ የኃይል አቅርቦቶችን አቋርጠዋል። የሰሜን ምስራቅ ዩክሬን ቮልይን ግዛት ባለስልጣናት እንደገለጹት በኃይል መሰረተልማት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ባለስልጣናቱ በጦርነቱ ምክንያት የኃይል መሰረተልማቱ ያለበትን ሁኔታ ግልጽ ማድረግ አይፈልጉም።
በደቡብ ማይኮላይቭ ግዛት ደግሞ ሌሊቱን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡባዊቷ የዛፖሮዥያ ግዛት እና በጥቁር ባህሯ የወደብ ከተማ ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተከስተዋል።
"ሩሲያ ከባድ የተባለ የአየር ጥቃት ፈጽማለች። ድሮን እና ሚሳይሎች በሰላማዊ ከተሞች፣ በንጹሃን እና በኃይል መሰረተሌማቶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል" ብለዋል የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲቢሂያ።
ሚኒስትሩ ጥቃቱን ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ንግግር ላደረጉት ኦላፍ ሾልዝ መልስ ነው ሲሉ ገልጸውታል። የኔቶ አባል የሆነችው ፖላንድ ሩሲያ የምታስወነጭፋቸው ክሩዝ ሚሳይሎች ጥቃት እንዳያደርሱባት ለጥንቃቄ በአየር ክልሏ ውስጥ የጦር ጀት አሰማርታ እንደነበር ገልጻለች።