የሩዋንዳ አየር መንገድ ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዳይበር እገዳ ተጣለበት
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሩዋንዳ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠርታለች
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ M23 የተሰኘው አማጺ ቡድን በሩዋንዳ ይደገፋል የሚል እምነት አላት
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ ድንበር ላይ እንደሚንቀሳቀስ የሚገለጸው M23 የተሰኘው አማጺ ቡድን ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መበላሸት ምክንያት ሆኗል።
ይህ አማጺ ቡድን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቃቱን እያሰፋ የምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተሞችን በመቆጣጠር ላይ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
ቡድኑ ከዚህ በተጨማሪም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቅ እዝ ዋና ማዘዣ መቆጣጠሩን ተከትሎ ድርጊቱ ሀገሪቱን አሳስቧል።
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይህ አማጺ ቡድን ያለ ሩዋንዳ ድጋፍ አሁን የተቆጣጠራቸውን ቦታዎች ሊያዝ አይችልም ሲል ክስ አቅርቧል።
በፖል ካጋሜ የሚመራው የሩዋንዳ መንግስት በበኩሉ ከጎረቤቷ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች።
የሩዋንዳ ብሄራዊ ኩራት የሖነው ሩዋንዳ አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር ያገደችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኬንሻሳ የሀገሪቱ አምብሳደርን ለተጨማሪ ማራሪያ ጠርታለች።
ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪዎች ሩዋንዳ ከዚህ በፊት M23 የተሰኘው አማጺ ቡድንን እንደምትረዳ ገልጸዋል።
በዚህ አማጺ እና የመንግስት ወታደሮች መካከል እየተካሄደ ባለው በዚህ ጦርነት ምክንያት እስካሁን ከ72 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል።
ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዳይበር እገዳ የተጣለበት የሩዋንዳ አየር መንገድም በረራዎች በመሰረዛቸው ማዘኑን ገልጾ ከመንገደኞች የተቀበለውን የጉዞ ቲኬት ክፍያ እንደሚመልስ አስታውቋል።