በዲ.አር.ሲ. በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2000 በላይ ሆነ
በዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ (ዲ.አር.ሲ.) በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2000 በላይ ሲሆን በኢቦላ የተያዙ ደግሞ ከ3000 ሰዎች በላይ ማለፉን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱን የጤና ባለስልጣናት ጠቅሶ ሲጂቲኤን እንደዘገበው ከሆነ የኢቦላ ቫይረስ ከባለፈው ሀምሌ ወር ጀምሮ ከ2000 በላይ ሰዎችን ሲገድል፣ 341 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ አለባቸው ተብለው በመጠርጠራቸው እየተመረመሩ ነው፡፡
በአጠቃላይ እስከ አሁን ከ3000 በላይ ሰዎች በሀገሪቱ በኢቦላ ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
የኢቦላን ወረርሽኝን ለመቋቋም የተቋቋመውኮሚቴ ባካሄደው ቆጠራ መሰረት ነው በኢቦላ የሞቱና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ይፋ የሆነው፡፡
በምስራቃዊ ኮንጎ የሚገኙት ሁለቱ ግዛቶች ማለትም ሰሜን ኪቩ እና ኢቱሪ በከፍተኛ ትኩሳት መጋለጣቸውም ተነግሯል፡፡ በእነዚህ ግዛቶች ዉስጥ የኢቦላ የህክምና ማእከላትና በማእከሉ የሚገኙ ሰራተኞች በታጠ ኃይሎች በተለያየ ጊዜ የጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ቆይተዋል፡፡ ኢቦላን የመቆጣጠር ጥረት በአካባቢው ያሉ ታጣቂዎች በሚፈጥሩት ረብሻ በተደጋጋሚ ሲስተጓጎል ይስተዋላል፡፡
የአሁኑ የኢቦላ ወረርኝ በታሪክ እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2014 ተከስቶ 11,000 ሰዎችን ከገደለው ቀጥሎ ከባድ የሚባለው ነው፡፡