ዲአርሲ ወታደራዊ ኃይል “የኤም-23 አማጽያን በወታደራዊ ስፍራየ ላይ ጥቃት ፈጽመውብኛል” ሲል ከሰሰ
የኮነጎ ወታደራዊ ኃይል አማጽያኑን “ለአንዴና ለመጨረሻ ለማጥፋት የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ” መሆኑንም አስታውቋል
የኤም-23 ቡድን ከጥቃቱ ጀርባ ስለመኖሩና ከወታደራዊ ኃይሉ ጋር እየተዋጋ መሆኑን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ኃይል “የኤም-23 አማጺያን ቡዱን በወታደራዊ ስፍራ ላይ ጥቃት ፈጽመውብኛል”ሲል ከሰሰ፡፡
የኮንጎ ወታደራዊ ኃይል ጥቃት ተፈጽሞበታል ያለው ስፍራ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኘውን ሩትሹሩ የተሰኘ ወታደራዊ ስፍራ ነው፡፡ወታደራዊ ኃይሉ አማጽያኑን የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ውግያ እየተካሄደ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የወታደራዊ ስፍራው ምክትል አዘዥ ጀነራል ሲለቫይን ኢኬንግ " የኤም-23 አማጺ ብዱን በሩትሹሩ ወታደራዊ ስፋራ በሚገኙ የኮንጎ የታጠቁ ኃይሎች ላይ ጥቃት የፈጸመበት ዓላማ ግዛቱን በጸጥታ ችግር ለማተራመስ ነው፡፡ አሁን ውግያ እየተካሄደ ሲሆን ታጣቂ ኃይሎች የመጨረሻቸው ይሆናል"ብሏል፡፡
አማጺዎቹ ከሩትሹሩ በተጨማሪ በሰሜን ኪቩ ግዛት በሩዋንዳ እና በኡጋንዳ መካከል ባሉ ስልታዊ ኮረብታዎች በሩዋንዪ እና ቻንዙ ራቅ ባሉ መንደሮች ጥቃት ሰንዝሯልም ነው ያሉት ጀነራሉ።
ጦርነቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ወደ ዩጋንዳ እንዲሰደዱ ማድረጉንም የኡጋንዳ ቀይ መስቀል አስታውቋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ በቡናጋና ድንበር ላይ በኡጋንዳ መጠለያ ለማግኘት እየሰፈሩ እንደሚገኙም የኡጋንዳ ቀይ መስቀል ግለጸዋል።
የኮንጎ ወታደራዊ ኃይል ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚል ክስ ቢያቀርብም ግን፤ የኤም-23 ቡድን ከጥቃቱ ጀርባ ስለመኖሩና ከወታደራዊ ወይም ከመንግስት ጋር እየተዋጋ መሆኑን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
እንደ ደቡብ ሱዳን ካሉ ጎረቤት ሀገራት ግፍን በመሸሽ የሚመጡባትን 1.3 ሚሊዮን ስደተኞች በማስተናገድ የምትገኘው የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገረ ኡጋንዳ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም፡፡
ምስራቃዊ ኮንጎ በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ውስጥ የመንግስትን ተቃዋሚ አማጽያንን ጨምሮ በተቀናቃኝ ታጣቂ ቡድኖች መካከል በሚደረገው ጦርነት ለጸጥታ እጦት የተጋለጠ አከባቢ ነው።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በኡጋንዳ የሚገኝ አንድ የታጠቀ ቡድን በአካባቢው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚደርሰው ተከታታይ ጥቃት ተጠያቂ ነው ሲባል ይደመጣል።
ሶሞኑ በኮንጎ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፤በሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ‘ጎማ ከተማ’ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ሲያስጠነቅቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
አማጽያኑ እንደፈረንጆቹ 2012 በአቅራቢያው ያሉትን መሬቶች ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም በ2013 የተባበሩት መንግስታት ጦር በወሰደው እርምጃ አመአካኝነት ከአካባቢው ወደ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ መገፋታቸው የሚታወስ ነው።