ሩዋንዳ አማጺያንን በመደገፍ ግዛቴን ልትወር ነው ስትል ኮንጎ ክስ አቀረበች
የአፍሪካ ህብረትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ያሰጋኛል ማለቱ ይታወሳል
ዲአርሲ የሩዋንዳ ብሄራዊ ጦር ድንበር ጥሶ በመግባት ጥቃት ፈጽሞብኛል የሚል ክስ አቅርባ ነበር
ምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብክ ኦፍ ጎንጎ(ዲአርሲ) ባለስልጣናት እንደተናገሩት የሩዋንዳ ወታደሮችና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአማጺ ቡድን በመደገፍ የዲአርሲን ግዛት ለመውረር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
በጥቃቱ ምክንያት ከ25ሺ በላይ ሰዎቸ አካባቢቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት መሆኑን ተመድ አስታውቋል፡፡
ቀደም ሲል ዲአርሲ የሩዋንዳ ብሄራዊ ጦር ድንበር ጥሶ በመግባት ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚል ክስ አቅርባ ነበር፡፡
የሩዋንዳ ጦር በምስራቃዊ ኮንጎ በኩል እስከ ስድስት ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቆ መግባቱ ከኮንጎ አቻው ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሲልቬይን ኢክንጌ የሩዋንዳ ጦር ድንበራችንን አልፎ ተኩሶብናል ብለዋል፡፡የሁለቱ ሀገራት ጦር ወደ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው መሰደድ ጀምረው ነበር፡፡
ይሁንና የሩዋንዳ ጦር በከፈተው ተኩስ እስካሁን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን አዛዡ ተናግረዋል፡፡ሮይተርስ ግጭቱን አስመልክቶ ከሩዋንዳ ጦር በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጧል::
የኮንጎ ብሄራዊ ጦር ባደረገው የመልሶ ማጥቃት የሩዋንዳ ጦር አካባቢውን ለቆ ወጥቷል ተብሏል፡፡
በሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር መካከል ተመሳሳይ ግጭቶች የተከሰቱ ሲሆን ህፈወጥ ንግድ፤የአማቲያን ጥቃት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ግልጽ ድንበር አለመካለል ለሁለቱ ሀገራት ጦር መጋጨት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የአፍሪካ ህብረትም ከወራት በፊት ባወጣው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ያሰጋኛል ማለቱ ይታወሳል፡፡