ሩዋንዳ ከዘር ጭፍጨፋው በኋላ ምን አይነት ጊዜ እያሳለፈች ነው?
በጭፍጨፋው 800ሺ የሚጠጉ የቱትሲ ጎሳ አባላት ተገድለዋል
በሩዋንዳ በፈረንጆቹ 1994ዓ.ም በቱትሲ የጎሳ አባላት ላይ ሁቱዎች ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸው ነበር
ፕሬዝዳንቱ አፍሪካውያን የራሳቸውን ሃብት በሌሎች ከተመዘበረ በኋላ መልሰው ለማኝ የሚሆኑበት ሁኔታ ሊያበቃ ይገባልም ብሏል፡፡
እንደፈረንጆቹ በ1994 ቱትሲ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከትሎ ሀገሪቱ ከባድ ጊዜ ማሳለፏን ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በርካታ ወጣት ታዳሚያን በተገኙበት፤ ከእውቁ ጋናዊ ስራ ፈጣሪ ፍሬድ ስዋኒከር ጋር በኪጋሊ ባደረጉት ቆይታ ሩዋንዳ ካስተናገደችው ከባድ ቁስል ወጥታ ወደ ፊት ለመራመድ ስለተጓዘችባቸው ከባድ ወቅቶች አንስቷል፡፡
“ከዘር ማጥፋት ወንጀል በኋላ ከባዱ ነገር ከተጎጂዎች ጎን መቆም ነበር፡፡ ምክንያቱም ተጎጂዎቹ ከአጠገባቸው ያጡት ነገር ነበርና፡፡ ለኛ (ለአመራሮች) የሀገሪቱን ቀጣይ እጣ ፈንታ ለማስቀጠል ከነበረን በላይ፤ ተጨማሪ ለመስጠት የሚጠበቅብን ከባዱ ወቅት ነበር፡፡ ይህ ለአጥፊዎች ምንም ማለት አልነበረም፡፡ ምክንያቱም እነሱ ራሳቸውን ቀጣይ የሀገሪቱ የተሻሉ ዜጎች አድርገው እንዲያስቡ የሚጠየቁበት ወቅት ነበርና፡፡ ስለዚህ ጊዜው ለኛ በጣም የተወሳሰበና እንዴት ከተወሳሰበ ሁኔታ መውጣት እንዳለብን እጅጉን ያስጨነቀ ነበር፡፡” ሲሉም ትውስታቸው አስቀምጠዋል ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ፡፡
ግፍ የደረሰባቸው ሰዎች በካቢኔ ሳይቀር እንዲወከሉ ማድረግ እንዲሁም የተጎጆወችን ቁስል ለማከም የሚያስችሉ አሰራሮች መዘርጋት ሌላው የወቅቱ አመራር ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት ያደረገባቸው ተግባራት እንደነበሩም አንስቷል ፖል ካጋሜ፡፡
ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ የአፍሪካ ፖለቲካና ቀጣይ የአፍሪካውያን ተግባር ምን መሆን አለባቸው በሚል ዙርያም አስታየታቸው ሰንዝሯል፡፡
ፖል ካጋሜ የአፍሪካ ጉዞ ማሳለጥ ከተፈለገ “የሀገራት የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፍልስፍና ዜጎችን ከድህነት እንዲወጡ በማድረግ እና ያላቸውን ሀብት በተገቢው መንገድ በመጠቀም ዙርያ የሚያጠነጥን ከሆነ ነው” ብሏል፡፡
አፍሪካውያን የራሳቸውን ሃብት በሌሎች ከተመዘበረ በኋላ መልሰው ለማኝ የሚሆኑበት ሁኔታ ሊያበቃ ይገባልም ነው ያሉት፡፡ፖል ካጋሜ“ይህ አስተሳሰብ ነው በአፍሪካ መለወጥ ያለበት ፤ደሞም ይቻላል”ም ብሏል፡፡