ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ በዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች የአስገድዶ መድፈር ድርጊት መበሳጨቷን ገለጸች
ኢቦላን ለመከላከል በሚል ወደ ዲአርሲ የገቡ ሰራተኞች 63 ህጻናትን እና ሴቶችን ደፍረዋል ተብሏል
በህጻናት እና ሴቶች አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተጠረጠሩ የዓለም ጤና ደርጅት ሰራተኞች ቁጥር 80 ደርሷል
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ በዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች የአስገድዶ መድፈር ድርጊት መበሳጨቷን ገለጸች።
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ነበር የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው የላከው።
ባለሙያዎቹ በፈረንጆቹ ከ2018 አስከ 2020 ዓመት ድረስም ኢቦላ ወረርሽኝን እንዲከላከሉ ከተላኩት ከ80 በላይ የሚሆኑን የድርጅቱ ሰራተኞች ህጻናትን እና ሴቶችን አስገድደው እንደደፈሩ ሲጂቲኤን አፍሪካ አንድ በጉዳዩ ዙሪያ የተሰራ ጥናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
- የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ቴድሮስ(ዶ/ር) በድርጅቱ ሰራተኞች ሴቶች በመደፈራቸው “አዝኛለሁ” አሉ
- ቻይና የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና መነሻን ለማጥናት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በዚህ አገር እድሜያቸው ከ13 እስከ 43 ዓመት የሚሞሉ ህጻናት እና ሴቶች ስራ እናስቀጥራችኋለን በሚል ተደፍረዋል።
በዚህ የአስገድዶ ደፈራ እና ጾታዊ ትንኮሳ ወንጀል ላይ በድምሩ 80 የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች መሳተፋቸው ድርጅቱ ባስጠናው ጥናት መረጋገጡም ተገልጿል።የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ማዘናቸውን ገልጸው የድርጊቱ ሰለባ የሆኑትን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።
የዲአርሲ ሰብዓዊ መብት ሚኒስትር አልበርት ፑዌላ በጉዳዩ ላይ