የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና መነሻን ለማወቅ የሚደረገውን ጥናት ከፖለቲካ ጋር ማያያዝ እንዲቆም ጠየቀ
ድርጅቱ አባል ሀገራት የኮሮና ቫይረስ መነሻ ፍለጋን ከፖለቲካ ጋር ማያያዝ እዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሁሉም መንግስታት የኮሮና ቫይረስ መነሻ ፍለጋን ከፖለቲካ ጋር ማያያዝ እንዲያቆሙና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል አንድ የጋራ ማእቀፍ እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በመጋቢት 2021 የሳርስ ኮቪድ2 ቫይረስ አመጣጥ ላይ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የቻይና የጋራ ሪፖርት ከታተመ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት መደረግ ያለባቸውን ቀጣይ ተከታታይ ጥናቶች ዘርዝሯል እናም ውይይቶችም ውስጥ ይቀጥላል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ወደፊት ተከታታይ ጥናት እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ቅድሚያ የሚሰጠው ሳይንቲስቶች በመጀመሪያው የጥናት ምዕራፍ ላይ እንዲገነቡ ፣ በፈረንጆቹ በመጋቢት 2021 ሪፖርት የተዘረዘሩትን የውሳኔ ሃሳቦች መተግበር እና በሁሉም መላምቶች ላይ ሳይንሳዊ ጥረቶችን ማፋጠን ነው ብሏል መግለጫው።
ድርጂቱ ቻይና የኮሮና ቫይረስ መነሻን በተመለከተ ሚደረገው ጥናት ተባባሪ አይደለችም በማለት ቅሪታውን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡የኮሮና ወረርሽኝ በፈረንጆቹ 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በቻይናዋ ሁቤ ግዛት ሲሆን ወደ ተለያዩ አለም ሀገራት በመስፋፋት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ቀውስ አስከትሏል፡፡