ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ሊወዳደሩ ነው
ዋና ዳይሬክተሩ በአፍሪካ ድጋፍ እንዳላቸው ቢነገርም “ከኢትዮጵያ ድጋፍ ያገኙ ይሆን..?” የሚል ጥያቄ ግን ፈጥረዋል
የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19ን ለመታገል ያደረገውን ርብርብ ዶ/ር ቴድሮስ ጎልተው የወጡበት ነው ተብሏል
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም የድርጅቱን ሀላፊ ሆነው ለቀጣይ አምስት አመታት ለምምራት በሚያስችላቸው የሁለተኛ ዙር ውድድር ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ሮይተርስ ስቴት ኒውስን ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል፡፡
በፈረንጆቹ በ2019 መገባደጃ ላይ አዲሱ የ SARS-CoV-2 ቫይረስ በማዕከላዊ ቻይናዊቷ ውሃን ከተማ መከሰቱን ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመታገል በሚያደርገው ትግል ዶ/ር ቴድሮስ ጎልተው ወጥተዋል፡፡
አሁን ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ዙር በሚወዳደሩበት ወቅት “በሌሎች ተቀናቃኞች ይፈተኑ ይሆን?” ለሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ለሁለተኛ ዙር በሚያደርጉት ውድድር ከአፍሪካ ሀገራት ወሳኝ ድጋፍ እንደሚያገኙ ከወዲሁ ቢገመትም ከሀገራቸው ኢትዮጵያ ድጋፍ ልያገኙ ስለመቻላቸው ግን እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ሮይተርስ ዲፕሎማቶች ነግረውኛል ሲል ዘግበዋል፡፡
ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ግጭት ጉዳይ ዋና ዳይሬክተሩ ለቀድሞ ድርጅታቸው ህወሀት ወግነዋል እንዲሁም ለትግራይ መንግስት የዲፕሎማሲ ድጋፍ አድረገዋል በማለት ከሷቸዋል፡፡
ባለተጠበቀ ሁኔታ የዓለም አቀፍ ዝናቸውን ከፍ ያለው ዋና ዳይሬክተሩ ዋና ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም፤ ኮሮና ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ ነው ተብሎ ከመፈረጁ በፊት በወርሀ ጥር 2020 ወደ ቻይና እቅንተው ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች መምከራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ይሁን እንጅ ይህ አካሄድ በቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አልተወደደላቸውም ነበር፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስን "አፍቃሬ-ቻይና" ናቸው በሚል ክስ፤ አሜሪካ በድርጀቱ የነበራትን ሚና እንድትገታ ውሳኔ አሳልፈው እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡ ምንም እንኳ አሁን ላይ የትራምፕ ውሳኔ በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ቢቀለበስም፡፡