የኮንጎው “ሩምባ ዳንስ” በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዘገበ
ሩምባ በቅርስነት መመዝገቡ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በኮንጎ ብራዛቪል ከፈተኛ ደስታ ፈጥሯል
የኮንጎው ዘመናዊ የሩምባ ዳንስ 100 አመት አስቆጥሯል ተብሏል
የኮንጎው ሩምባ ዳንስ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካከቱ የተባበሩት መንግስታት የባህል ኤጀንሲ/ዩኔስኮ/ ባደረገው ስብሰባ ማጽደቁ አስታወቀ፡፡
የሩምባ ዳንስ በቅርስነት መመዝገቡ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በኮንጎ ብራዛቪል ህዝቦች ዘንዳ ከፈተኛ ደስታ እንደፈጠረም ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የሁለቱ ሀገራት የጋራ መለያ የሆነው ሩምባ ዳንስ በውስጡ የኩባ ሩምባ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የፖሊፎኒክ ሙዚቃ እና የቡሩንዲ ከበሮ የተቀላቀሉበት ነው።
ናፍቆትን፣ የባህል ልውውጥን፣ መቋቋምን፣ መቻልን እና ደስታን በሚያሳይ መልኩ በማራኪ የአለባበስ ኮድ የሚቀርብ ዳንስም ነው ሩምባ፡፡
የዩኔስኮ ዜና በመጠባበቅ ላይ የነበሩት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ "እነዚህ ከኮንጎ የተገኙ እና ወደ ዓለም የተላኩ ውድ ሀብቶች የኩራታችን አካል ናቸው" በማለት ባለፈው ሳምንት በትዊተር ገፃቸው ላይ አጋርተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
"ሩምባን ማስተዋወቅ የጋራ ግዴታችን ነው"ም ሲሉም አክሏል።
ስፔሻሊስቶች፡ የሩምባን አመጣጥ ሲገልጹ በጥንታዊው የመካከለኛው አፍሪካ እና በኮንጎ ግዛት ውስጥ ይገኙ የነበረ ሰዎች "ንኩምባ" የተባለ ዳንስ ይለማመዱ እንደነበር ያነሳሉ፡፡
ንኩምባ የሚለው ቃል እምብርት ማለት ሲሆን ወንድና ሴት እምብርታቸው ከሌላው ሰው በተቃራኒ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ነው።
አፍሪካውያን በባሪያ ንግድ አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው ሙዚቃቸውን እና ባህላቸውን አምጥተው በመጨረሻ በሰሜን አሜሪካ ጃዝ እና በደቡብ አሜሪካ ራምባ መውለዳቸውንና ፤ከዚያም ነጋዴዎች ሙዚቃውን በሪከርድ እና ጊታር ወደ አፍሪካ ማምጣታቸውም ይነገራል።
በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ የሚገኘውን የዲ.አር.ሲ ብሄራዊ የስነጥበብ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አንድሬ ዮካሊ “ዘመናዊው የሩምባ ዳንስ 100 አመት አስቆጥሯል” ብሏል፡፡