በምስራቃዊ ኮንጎ ታግተው የነበሩ የአለምአቀፍ ቀይመስቀል ማህበር ሰራተኞች ተለቀቁ
ኃላፊዋ ሰራተኞቹ ከእገታ እንዳመለጡ የሰጡት ማብራሪያ የለም፡
ማህበሩ የሰብአዊ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የሚደረገው እገታ ሌላ ጥቃት፣ በግጭት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የሚደረገውን እንቅስቃሴ አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል
በምስራቃዊ ኮንጎ ታግተው የነበሩ ሁለት የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ሰራተኞች መለቀቃቸውን ማህበሩ ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ባለፈው ህዳር ወር አንድ ኮንጎዊ እና አለምአቀፍ ስራተኛ ከአስር በላይ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት የሰሜን ኮቩ ግዛት መታገታቸው ማህበሩ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር በኮንጎ ኃላፊ ሰራተኞቹ በመለቀቃቸው የእረፍት ስሜት እንደተሰማቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመቀላቀላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሰብአዊ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የሚደረገው እገታ ሌላ ጥቃት፣ በግጭት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የሚደረገውን እንቅስቃሴ አደጋ ላይ ይጥላል ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ ሰራተኞቹ እንዴት እንደታገቱን እንዴት ከእገታ እንዳመለጡ የሰጡት ማብራሪያ የለም፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በምስራቅ ኮንጎ በእርዳታ ሰራተኞች ላይ የሚደረዱ ጥቃቶች ሊጨምሩ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡ በዚሁ በምስራዊ ኮንጎ ግዛት የተመድ የስተደኞች ኤደንሲ ሰራተኞች ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውቋል፡፡