ኡጋንዳ እና ኮንጎ በጽንፈኛ ሚሊሻዎች(ኤዲኤፍ) ላይ የጋራ ጥቃት ጀመሩ
ሀገራቱ የጋራ ወታደራዊ ጥቃት የሰነዘሩት በሰሜን ኪቩ ግዛት እና በምስራቅ ኮንጎ አዋሳኝ አካባቢዎች ነው ተብሏል
ኤዲኤፍ በጽንፈኛ የታጣቂዎች ቡዱኑ ህዳር 16 በኡጋንዳ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ የሚታወስ ነው
ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ በምስራቅ ኮንጎ የሚገኙት እንዲሁም ከአስላማዊ መንግስት ጋር እንደሚተባበሩ የሚነገርላቸውና የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች(ADF) በመባል የሚታወቀውን አማጺ ቡዱን ላይ የጋራ ወታደራዊ ጥቃት መሰንዘራቸው አስታወቁ፡፡
የኮንጎ መንግስት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ “ከኡጋንዳ ጦር ጋር የታለመው እና የተቀናጀ እርምጃ ዛሬ ተጀምሯል፤ ኡጋንዳም በአሸባሪዎች ላይ የአየር እና መድፍ ድብደባ አካሂዳለች”ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባጋሩት ጽሁፍ ገልጿል፡፡
በሰሜን ኪቩ ፤በዋታሊንጋ ግዛት በምስራቅ ኮንጎ አዋሳኝ አካባቢዎች ዛሬ ጠዋት ፍንዳታዎች እንደተሰሙ የአከባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲልም ሮይተረስ ዘግቧል፡፡
በአከባቢው ከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት እንዳለ የገለጡት ነዋሪዎቹ “ቤተሰባችንን በጨፈጨፈውን ታጣቂ ኃይል ብዙ ተሰቃይተናል፤ መፍትሄ እንዲመጣ እየጠበቅን ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ጦር በተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር እንደሚታገዝ የሚታወቅ ነው፡፡
በውድ ማዕድናት የበለጸገችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ ጦር እና የሰላም አስከባሪው ከወራት በፊት በአማጺው የኤዲኤፍ ቡዱን በወሰዱት እርምጃ በርካታ ታጣቂዎች ገድለው ነበር፡፡
የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች(ADF) አማጺ ቡድን በፈረንጆቹ 1990 መጀመሪያ ዓመት አንስቶ በኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀስ ሲሆን በኡጋንዳ ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀ ነው።
አማጺ ቡድኑ በተለያዩ ጊዜያት በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ሃላፊነት በመውሰድ ይታወቃል።
ጽንፈኛው የታጣቂዎች ቡዱኑ ህዳር 16 በኡጋንዳ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ የሚታወስ ነው፡፡
በተጨማሪም በጥቅምት 23 በካምፓላ አቅራቢያ በሚገኝ የአሳማ ሥጋ ሬስቶራንት ውስጥ አንዲት አስተናጋጅ ለገደለው ጥቃት እና በጥቅምት 8 ለተፈጸመውና ማንንም ያልጎዳው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱ ይታዋል፡፡