እያሽከረከራት የነበረችውን መኪና ከኃይት ሀውስ መግቢያ በር ጋር ያጋጨው አሽከርካሪ ህይወቱ ማለፉን ባለስልጣናት ተናግረዋል
ከኃይት ሀውስ መግቢያ በር ጋር የተጋጨው አሽከርካሪ ህይወቱ አለፈ።
በትናንትናው እለት እያሽከረከራት የነበረችውን መኪና ከኃይት ሀውስ መግቢያ በር ጋር ያጋጨው አሽከርካሪ ህይወቱ ማለፉን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አሽከርካሪው መኪናው ውስጥ ሞቶ መገኘቱን የአሜሪካ ሰክሬት ሰርቪስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሰክሬት ሰርቪስ እንገደለጸው ከውጨኛው የኋይት ኃውስ በር ጋር የተጋጨው አሽከርካሪው "በከፍተኛ ፍጥነት ሲያበር ነበር"። በቦታው የነበሩ የጸጥታ አካላት አሽከርካሪውን ከመኪናው ውስጥ አውጥተው ሊረዱት ቢሞክሩም፣ በህይወት አላገኙትም።
አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን የገለፈጸው ሰክሬት ሰርቪስ ለኃይት ሀውስ የሚያሰጋ ነገር የለም ብሏል።የዲሲ ፖሊስ ዲፓርትመንት በበኩሉ የአሽከርካሪው ማንነት አለመታወቁን ገልጿል።
ሰክሬት ሰርቪስ አጠቃላይ ክስተቱን መመርመሩን እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን የዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት ደግሞ "ይህን ከባድ አደጋ" ያጣራል ተብሏል።
የሰክሬት ሰርቪስ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አንቶኒ ጉግሌልሚ በኤክስ ገጻቸው ግጭቱ በደረሰበት ቦታ ፖሊስ እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ምርመራ እያካሄዱ ስለነበሩ የትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ተደርጎ ነበር ብለዋል።