ድሮግባ የአፍሪካ ተጫዋቾችን ስለሀሰተኛ ወኪሎች ሊያስተምር ነው
ድድየር ድሮግባ ከፊፍፕሮ እና አይኤልኦ ጋር በመሆን ለአፍሪካውያን ተጫዋቾች ስለ ሀሰተኛ ወኪሎች (ፌክ ኤጀንቶች) ሊያስተምር መሆኑ ተገልጿል
ፊፍፕሮ በርካታ ተጨዋቾች ኤጀንት ሳይሆኑ "ኤጀንት ነን" የሚሉ ሰዎች ቀርበዋቸው እንደነበር መረዳት መቻሉን ገልጿል
ድድየር ድሮግባ ከፊፍፕሮ እና አይኤልኦ ጋር በመሆን ለአፍሪካውያን ተጫዋቾች ስለ ሀሰተኛ(ፌክ ኤጀንቶች) ሊያስተምር መሆኑ ተገልጿል።
የቀድሞ የቸልሲ አጥቂ ድድየር ድርግባ የአፍሪካ ተጨዋቾች ብዙ ጊዜ ዝነኛ ትሆናላችሁ እያሉ ቃል በሚገቡ ፌክ አጄንቶች እጅ እየወደቁ ነው ብሏል።
ድሮግባ በራሱ ፋውንዴሽን በኩል ከአለም አቀፍ የእግርኳስ ክለቦች ህብረት እና አለምአቀፍ የሰራተኞች ማህበር ጋር በትብብር ስለችግሩ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ ነው።
ድሮግባ "እባካችሁ ይህንን እንድትሰሙት እፈልጋለሁ" ሲል በአኒሜሽን ቪዲዮ ለተጨዋቾች መልእክት አስተላልፏል።
"ማንን ማመን እንዳለባችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ገንዘባችሁን የሚፈልግ ሰው በፍጹም አትመኑ" ብሏል ድሮግባ።
ፊፍፕሮ በቅርቡ ከሰባት የአፍሪካ ሀገራት በመጡ 263 ተጨዋቾች ላይ ባስጠናው የዳሰሳ ጥናት 70 በመቶ የሚሆኑት በፌክ ኤጀንቶች ወድቀው እንደነበር ገልጿል።
ፊፍፕሮ እንደገለጸው 43 በመቶ የሚሆኑ ተጨዋቾች ለሙከራ፣ ለክለብ ለመፈረም 39 በመቶ ተጨዋቾች ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም 56 በመቶ የሚሆኑት ቃል የተገባላቸውን ሙከራ ያላገኙ ሲሆን 44 በመቶዎቹ ደግሞ አልተፈራረሙም።
ፊፍፕሮ በርካታ ተጨዋቾች ኤጀንት ሳይሆኑ "ኤጀንት ነን" የሚሉ ሰዎች ቀርበዋቸው እንደነበር መረዳት መቻሉን ገልጿል።
ድርግባ እንዳለው ኤጀንት ለማግኘት ስለሚጓጉ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ ብሏል።
"የእናንተ ምርጥ ኤጀንት ልታምኑት የምትችሉት ሰው ሳይሆን የእናንተ ምርጥ ኤጀንት ችሎታችሁ ነው" ነው ሲል ድሮግባ ተናግሯል።
ፊፋ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት ከህዳር 2023 ጀምሮ እያንዳንዱ ኤጀንት ፈተና ወስዶ የፊፋን ፍቃድ መያዝ ይኖርበታል ይላል።
ድሮግባ ያስተላለፈው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ቪዲዮ ፌክ ኤጀንት እንዴት መለየት እንደሚቻል፣ ኮንትራት እንዴት እንደሚገኝ እና ተጨዋቾች እንደ ውጭ ተቀጣሪዎች ስለሚኖራቸው መብት የሚያስረዳ ማስታወሻም ተለቋል።
ችግሩ የአንድ ወይም የሁለት ተጨዋቾች ጉዳይ ሳይሆን የሺዎች ነው ሲል ድሮግባ የችግሩን አሳሳቢነት ተናግሯል።