በሕንድ ከባድ የአየር ብክለት መከሰቱን ተከትሎ ሰራተኞች በቤት ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ
በሕንድ በደረሰ የአየር ብክለት ምክንያት ተምህርት ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ተቋሟት ተዘግተዋል
በሕንድ መዲና ኒው ዴልሂ ከባድ የአየር ብክለት በመከሰቱ የአገሪቱ ፍርድ ቤት ሰራተኞች በቤታቸው እንዲሰሩ ወስኗል
በሕንድ ከባድ የአየር ብክለት መከሰቱን ተከትሎ ሰራተኞች በቤት ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ፡፡
የሕንድ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ በተለይም የተለያዩ ተቀጣጣይ ነገሮችን በማጨስ የሚከበረው የሂንዱ ፌስቲቫል ወይም ዲዋሊ ከተከበረ በኋላ ከተማይቱ እና ዙሪያዋ በመርዛማ አየር ተሸፍናለች፡፡
በዚህ የተበከለ አየር ምክንያት ብዙዎች ለተለያዩ የመተንፋሻ በሽታዎች ህመም መጋለጣቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
የኒው ዴልሂ እና አካባቢዋ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የተበከለውን አየር መጠን ለመቀነስ ሰራተኞች በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ወስኗል፡፡
በህንድ ጎርፍ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት በትንሹ 125 ሰዎች ሞቱ
ሕንድ ባጋጠማት የአየር ብክለት ምክንያት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን ለጊዜው የዘጋች ሲሆን በተለይም ለአየር ንብረት ብክለቱ አባባሽ ይሆናሉ የተባሉት ስራ እንዲያቆሙ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
የኒው ዴልሂ ‘ኤር ኳሊቲ ኢንዴክስ’456 ሲሆን ይህም የብክለቱ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና ጤናማ ሰዎችንና ታማሚዎችን እንደሚጎዳ ነው የተነገረው፡፡
‘ኤር ኳሊቲ ኢንዴክስ’ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር አየር ውስጥ የካርዲዮቫስኩላር እና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን እንደ የሳንባ ካንሰር ሊያስከትል የሚችለውን የመርዛማ ብናኝ መጠን ይለካል፡፡
በህንድ ውስጥ በየዓመቱ መርዛማ አየር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ይገድላል፤ በሀገሪቱ ውስጥ በሰሜናዊ ክልሎች እና በ20 ሚሊዮን ህዝብ ዋና ከተማ ላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ያስከትላል።