የህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ በመርዛማ አየር መሸፈኗ ተገለጸ
ነዋሪዎች በዴልሂ ውስጥ ስላለው አደገኛ ሁኔታ ቅሬታ አቅርበዋል
በህንድ በየአመቱ በአየር ብክለት ምክንያት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል
የህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ፤የሂንዱ ፌስቲቫል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው በመርዛማ የአየር ተሸፍናላች፤የአየር ብክለትም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡
የህንዱ ፌስቲቫል አክባሪዎች የአየር ንብረቱን ሊያዛቡ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠቡ ቢጠየቁም፤ አክባሪዎቹ ግን እግዱን አለመቀበላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኒው ዴልሂ ኤየር ኳሊቲ እንዴክስ 456 ሲሆን ይህም የብክለቱ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና ጤናማ ሰዎችንና ህምም ያለባቸውን በጽኑ ይጎዳል ተብሏል፡፡
ኤየር ኳሊቲ እንዴክስ(አይ ኪውአይ)፣ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር አየር ውስጥ የካርዲዮቫስኩላር እና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን እንደ የሳንባ ካንሰር ሊያስከትል የሚችለውን የመርዛማ ብናኝ መጠን ይለካል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አንዳንድ ነዋሪዎች በዴልሂ ውስጥ ስላለው አደገኛ ሁኔታ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ የኒው ዴልሂ የአየር ብክለት ከአለም ከተሞች መጥፎ የሚባልናብዙውን ጊዜ በክረምት መጀመሪያ ላይ ዓመታዊ ጭማሪ መኖሩ ተዘግቧል፡፡
"በየቀኑ ጭስ እየተነፈስን ነው። ሚዲያ ስለ ጉዳዩ ይነጋገራል፣ መሪዎች እያስተካከሉ ነው ይላሉ። በሚቀጥለው አመት ሄዶ ተመልሶ ይመጣል።”ብለዋል ሮይተርስ ያነጋገራቸው የዴልሂ ነዋሪ፡፡
በህንድ ውስጥ በየዓመቱ መርዛማ አየር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ይገድላል፤ በሀገሪቱ ውስጥ በሰሜናዊ ክልሎች እና በ20 ሚሊዮን ህዝብ ዋና ከተማ ላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ያስከትላል።