ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ በመከላከያ ስትራቴጂዋ ላይ የሚመክር ቁልፍ ስብሰባ እያካሄደች መሆኑን ገለጸች
ባለፈው ወር ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወታደራዊ የስለላ ሳተላይት የማስወንጨፍ ሙከራ አድርጋ ነበር
የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ ውጥረቱን እንደሚያባብሰው ሰሜን ኮሪያ ገልጻለች
ሰሜን ኮሪያ የዲፕሎማሲ እና የመከላከያ ስትራቴጂዋ እየተቀየረ ካለው የአለም ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የሚያስችል ወሳኝ የፖርቲ ስብሰባ እያካሄደች መሆኑን አስታውቃለች።
በስበስባው የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተሳትፈዋል።
የሀገሪቱ ሚዲያ ኬሲኤን እንደዘገው ይህ ሰፊ ስብሰባ በአመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ያለውን የምጣኔ ሀብት ስራዎችንም ይገመግማል ተብሏል።
ስብሰባው ለበርካታ ቀናት እንደሚቆይ ይጠበቃል።
ሰሜን ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የሚያደርጉትን ደቡብ ኮሪያን እና አሜሪካን ካስጠነቀቀች ከአንድ ሰአት በኋላ ሁለት የአጭር ርቀት ሚሳይሎችን ወደ ምስራቅ ጠረፍ አስወንጭፋለች።
የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ ውጥረቱን እንደሚያባብሰው ሰሜን ኮሪያ ገልጻለች።
ባለፈው ወር ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወታደራዊ የስለላ ሳተላይት የማስወንጨፍ ሙከራ አድርጋ ነበር። ነገርግን ሳተላይቷ የተወነጨፈችባት ሮኬት ሞተር ብልሽት ምክንያት ሳይሳካላት ቀርቷል።