ድቪ ሎተሪ ሲሞላ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ስህተቶች ምን ምን ናቸው?
የድቪ 2025 ማመልከቻ ጊዜ እስከ ጥቅምት 27 ድረስ ይቆያል ተብሏል
አሜሪካ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በእጣ ከተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ትወስዳለች
ድቪ ሎተሪ ሲሞላ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ስህተቶች ምን ምን ናቸው?
የዓለማችን ልዕለ ሀይል ሀገር አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ወይም ድቪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ትወስዳለች። ከነዚህ 50 ሺህ የድቪ እድለኞች ውስጥ እስከ 40 ሺህ ያህሉ አፍሪካዊያን ናቸው፡፡
ኢትዮጵያዊያን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻን በብዛት ከሚሞሉ መካከል ዋነኞቹ ሲሆኑ በየዓመቱ በአማካኝ ከ2 ሺህ እስከ 4 ሺህ ድረስ የእድሉ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ይገለጻል፡፡
የ2025 የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ጊዜ ካሳለፍነው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት የሆነ ሲሆን እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ስህተቶች ምን ምን ናቸው? የሚሉትን እንደሚከተለው አዘጋጅተንላችኋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን አመልካቾችን ጨምሮ በመላው ዓለም ከሚፈጸሙ ስህተቶች መካከል የመጀመሪያው ስምን እና የልደት ቀንን በትክክል አለመሙላት ነው፡፡ በነዚህ ስህተቶች ምክንያት በየዓመቱ በርካቶች የድቪ እድለኞች ቢሆኑም በመጨረሻም ቪዛ ለመከልከላቸው ዋነኛው ምክንያት ይሆናል፡፡
የጽዳት ሰራተኞቹ አዋጥተው በገዙት ቲኬት የ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸነፉ
ሁለተኛው ተደጋጋሚ የሚፈጸመው ስህተት የድቪ ማመልከቻን ከአንድ ጊዜ በላይ መሙላት ሲሆን ማመልከቻዎትን ከአንድ ጊዜ በላይ ከሞሉ ማመልከቻዎ ውድቅ ይደረጋል፡፡
ትክክለኛውን የድቪ ሎተሪ ማመልከቻ ድረገጽ አለመጠቀም ሌላኛው በተደጋጋሚ የሚፈጸም ስህተት ሲሆን የሶስተኛ ወገን ድረገጽን ተጠቅመው ማመልከት የለቦትም፡፡
አራተኛው ተደጋጋሚ ስህተት የድቪ ማመልከቻ ፎርምን በሌላ ሰው ማስሞላት ሲሆን ይህም ለተለያዩ ስህተቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ የድቪ ማመልከቻዎትን ራስዎ ቢሞሉ የተሻለ ይሆናል፡፡
እንዲሁም የድቪ ማመልከቻ ሲሞላ ሙሉ የቤተሰብን ሁኔታ አለመሙላት አምስተኛው ተደጋጋሚ ስህተት ሲሆን በተለይም የባል ወይም ሚስት ስም፣ የልጆች ስም እንዲሁም የትዳር ሁኔታን በትክክል አለመሙላትም የድቪ እጣ ቢደርስዎትም ቪዛ ሊያስከለክልዎ ስለሚችል በትክክል ስለ መሙላትዎ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
ሌላኛው በአመልካቾች የሚፈጸም ተደጋጋሚ ስህተት ደግሞ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ አለመጠቀም ሲሆን ማመልከቻዎትን ሲሞሉ ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ መያዝዎን ያረጋግጡ፡፡